Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የሊባኖስ ዛፎች ስለ ወደቁ፥ እናንተ የዝግባ ዛፎች “ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ፤ ግርማ የነበራቸው ዛፎች ሁሉ ጠፍተዋል፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ስለ ተቈረጠ የባሳን ወርካዎች “ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የጥድ ዛፍ ሆይ፤ ዝግባ ወድቋልና አልቅስ፤ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋል! የባሳን ወርካዎች ሆይ፤ አልቅሱ፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯል!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋልና አልቅሱ! እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና አልቅሱ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፣ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፥ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 11:2
12 Referencias Cruzadas  

“የሰው ልጅ ሆይ! ወደ ደቡብ ፊትህን አዙረህ በደቡብ ላይ ተናገር፤ በደቡብ በኩል ባለው ጫካ ላይም ትንቢት ተናገርበት።


መቅዘፊያዎችሽ የተሠሩት ከባሳን በተገኘ የወርካ ዛፍ ነው፤ ወለልሽም የተሠራው ከቆጵሮስ በተገኘ ልዩ በሆነ የጥድ ሳንቃ ነው፤ ዙሪያውም በዝሆን ጥርስ ተለብጦአል።


በጥላው ሥር የነበሩትና ከሕዝቦች መካከል ተባባሪዎቹ የነበሩት በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ።


የእስራኤል ሕዝብ ርዳታቸውን ፈልጎ ወደ መሪዎቹ ይመጣል፤ እነርሱ ግን በጽዮን ተዝናንተው ስለሚቀመጡና በሰማርያ ተራራ ላይ ያለ ሥጋት ስለሚኖሩ ለእነዚህ ታዋቂ መሪዎች ወዮላቸው!


ሊባኖስ ሆይ! እሳት ዛፎችሽን ያቃጥል ዘንድ በሮችሽን ክፈቺ!


እረኞች ለምለም የሆነ መሰማሪያቸው ስለ ወደመ “ዋይ!” እያሉ ሲያለቅሱ ስሙ፤ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ ያለው የደን መኖሪያቸው ስለ ተደመሰሰ፥ አንበሶች በሐዘን ሲያገሡ ስሙ።


እንግዲህ ይህ ሁሉ ነገር በእርጥብ እንጨት ላይ የሚደረግ ከሆነ በደረቅ እንጨት ላይማ ምን ይደረግ ይሆን?”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos