Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 46:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሠራ​ዊ​ትም በኀ​ይል ይዘ​ም​ቱ​ባ​ታ​ልና፥ እንደ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችም በም​ሳር ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ድም​ፅዋ እን​ደ​ም​ት​ሸሽ እባብ ይተ​ማል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ ግብጽ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣ መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “ጠላቶችዋ በኃይል ዘምተው እንደ እንጨት ቈራጮች በምሳር ይመጡባታልና በደረቱ እንደሚሽሎኮሎክ እባብ ድምፅ ታሰማለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22-23 የጠላት ሠራዊት ኀይል ሲቃረብ ግብጽ እንደ እባብ የፉጨት ድምፅ እያሰማች ትሸሻለች፤ ሰዎች ጥቅጥቅ ያለውን ደን እንደሚመነጥሩ በመጥረቢያ አደጋ ይጥሉባታል። የሰዎቻቸው ብዛት በቊጥር አይደረስበትም፤ የወታደሮቻቸውም ብዛት ከአንበጣ ሠራዊት ይበልጣል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከሠራዊትም ጋር ይሄዳሉና ድምፅ እንደ እባብ ይተምማል፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 46:22
13 Referencias Cruzadas  

ነገ​ር​ሽም በም​ድር ውስጥ ይሰ​ጥ​ማል፤ ቃል​ሽም ከም​ድር በታች እን​ደ​ሚ​ና​ገር ይሆ​ናል፤ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ቃል​ሽም በም​ድር ውስጥ ዝቅ ይላል።


የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፦ አንተ ከተ​ዋ​ረ​ድህ ጀምሮ ማንም ይቈ​ር​ጠን ዘንድ አል​ወ​ጣ​ብ​ንም ብለው በአ​ንተ ደስ አላ​ቸው።


የጥድ ዛፍ ሆይ፥ ዝግባ ወድቆአልና፥ ከበርቴዎችም ጠፍተዋልና ዋይ በል፣ እናንተም የባሳን ዛፎች ሆይ፥ ጽኑው ጫካ ተቈርጦአልና ዋይ በሉ።


አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥


ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፥ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፥


አን​ተም በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ በኩል እን​ዲህ ብለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ራስ ወጥ​ቻ​ለሁ፤ ረዣ​ዥ​ሞ​ቹ​ንም ዝግ​ባ​ዎች፥ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ከፍ​ታ​ውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገ​ባ​ለሁ፤


“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”


አለ​ቆ​ቹም “አዳ​ን​ና​ችሁ፤ ለማ​ኅ​በ​ሩም እን​ጨት ትቈ​ር​ጡና ውኃ ትቀዱ ዘንድ መደ​ብ​ና​ችሁ” አሉ​አ​ቸው። አለ​ቆ​ቹም እን​ዲሁ አዘ​ዙ​አ​ቸው።


ቀን​ዳ​ች​ሁን እስከ አር​ያም አታ​ንሡ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን አት​ና​ገሩ።”


በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ የተ​ቀ​ጠሩ ሠራ​ተ​ኞች በእ​ር​ስዋ ተቀ​ል​በው እንደ ሰቡ ወይ​ፈ​ኖች ናቸው፤ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀንና የቅ​ጣ​ታ​ቸው ጊዜ መጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ተመ​ለሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሸሹ፤ አል​ቆ​ሙ​ምም።


ሊቈ​ጠሩ የማ​ይ​ችሉ የዱ​ር​ዋን ዛፎች ይቈ​ር​ጣሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከአ​ን​በጣ ይልቅ በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ቍጥ​ርም የላ​ቸ​ው​ምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios