እስራኤል ሆይ! አንቺ እንደ መከር መጀመሪያ ፍሬ ለእኔ የተለየሽ ነበርሽ፤ ለእኔም የተቀደስሽ ርስት ሆነሽ ነበር፤ ስለዚህም አንቺን መጒዳት በሚፈልጉት ሁሉ ላይ መከራና መቅሠፍት አመጣሁባቸው።’ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ያዕቆብ 1:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፍጥረቱ በኵራት እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለፍጥረቱ የበኵራት እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን። |
እስራኤል ሆይ! አንቺ እንደ መከር መጀመሪያ ፍሬ ለእኔ የተለየሽ ነበርሽ፤ ለእኔም የተቀደስሽ ርስት ሆነሽ ነበር፤ ስለዚህም አንቺን መጒዳት በሚፈልጉት ሁሉ ላይ መከራና መቅሠፍት አመጣሁባቸው።’ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምታጭዱበት ጊዜ የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ ስጡ፤
የእስራኤል ሕዝብ ርዳታቸውን ፈልጎ ወደ መሪዎቹ ይመጣል፤ እነርሱ ግን በጽዮን ተዝናንተው ስለሚቀመጡና በሰማርያ ተራራ ላይ ያለ ሥጋት ስለሚኖሩ ለእነዚህ ታዋቂ መሪዎች ወዮላቸው!
ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር።
እናንተም የመዳናችሁ መልካም ዜና የሆነውን የእውነት ቃል በሰማችሁ ጊዜ በክርስቶስ አምናችኋል፤ እንዲሁም እርሱ ሊሰጣችሁ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታትማችኋል።
የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያደርስና በሥራውም እንደማያፍር ሠራተኛ ሆነህ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብና ተቀባይነትን ለማግኘት ጥረት አድርግ።
ስማቸው በሰማይ ወደተጻፈው፥ የቤተ ክርስቲያን የበኲር ልጆች ወደሆኑት ወደ አማኞች ጉባኤ፥ የሁሉ ፈራጅ ወደ ሆነው አምላክና ፍጹምነትን ወዳገኙት የጻድቃን ነፍሳት ቀርባችኋል።
ስለዚህ ርኲሰትንና የክፋትንም ብዛት ሁሉ አስወግዳችሁ እግዚአብሔር በልባችሁ የተከለውንና ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።