Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እናንተም የመዳናችሁ መልካም ዜና የሆነውን የእውነት ቃል በሰማችሁ ጊዜ በክርስቶስ አምናችኋል፤ እንዲሁም እርሱ ሊሰጣችሁ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታትማችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፣ ይህም የድነታችሁን ወንጌል በሰማችሁ ጊዜ ወደ ክርስቶስ ተጨምራችኋል። አምናችሁም በርሱ በመሆን፣ ተስፋ ሆኖ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ታትማችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሁ፥ በክርስቶስም አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እና​ን​ተም ልት​ድ​ኑ​በት የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን የእ​ው​ነት ቃል ሰም​ታ​ች​ሁና አም​ና​ችሁ፤ ተስፋ ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ታተ​ማ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 1:13
38 Referencias Cruzadas  

የእርሱ ለመሆናችን ማስረጃ የሚሆን ማኅተሙን በእኛ ላይ ያደረገና ወደ ፊት ለእኛ ስለሚሰጠን ሀብት በልባችን መንፈስ ቅዱስን እንደ ዋስትና አድርጎ የሰጠን እርሱ ነው።


ለምትዋጁበት ቀን ማረጋገጫ እንዲሆናችሁ የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።


ነገር ግን “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ጸንቶ ይኖራል።


ደግሞም ስለ እናንተ ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ምክንያት አለን፤ ይኸውም ከእኛ የሰማችሁትን የእግዚአብሔርን ቃል በተቀበላችሁ ጊዜ በእናንተ በአማኞች የሚሠራውን ይህንን ቃል የተቀበላችሁት እንደ ሰው ቃል ሳይሆን ልክ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጋችሁ ነው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል ነው።


አብርሃም ገና ከመገረዙ በፊት እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደ ተቈጠረለት ማረጋገጫ ምልክት እንዲሆነው ተገረዘ፤ ስለዚህ አብርሃም፥ ሳይገረዙ ለሚያምኑና እምነታቸው ጽድቅ ሆኖ ለሚቈጠርላቸው ሁሉ አባት ነው።


እግዚአብሔር ሰውን የሚያድንበትን ጸጋውን ለሁሉም ገልጦአል፤


ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለአሕዛብ እንዲደርስና እኛም እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያለውን መንፈስ ቅዱስን በእምነት እንድንቀበል ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ በኋላ መንፈሴን በሰው ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፤ ወጣቶቻችሁም ራእይ ያያሉ።


እኔ በወንጌል ቃል አላፍርም፤ የወንጌል ቃል በመጀመሪያ አይሁድን፥ ቀጥሎም አሕዛብን፥ እንዲሁም የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሔር ኀይል ነው።


በእግዚአብሔር ቀኝ ለመቀመጥ ከፍ ባለ ጊዜና የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ከአብ በተቀበለ ጊዜ ይህን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።


አብ በእኔ ስም የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኳችሁንም ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል።


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


እነሆ! እኔ አባቴ የሰጣችሁን ተስፋ እልክላችኋለሁ፤ እናንተም ከላይ ኀይል እንደ ልብስ እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቈዩ።”


ተስፋ የማደርገው የአንተን ፍርድ ስለ ሆነ ዘወትር እውነት እንድናገር እርዳኝ።


እናንተ ቀድሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ናችሁ፤ ቀድሞ ምሕረት አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረት አግኝታችኋል።


እናንተ አስቀድሞ የኃጢአት ባሪያዎች ነበራችሁ፤ አሁን ግን ለተቀበላችሁት ትምህርት ከልብ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።


አብሮአቸውም በነበረ ጊዜ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “እኔ የነገርኳችሁን ከአብ የተሰጠ ተስፋ ጠብቁ እንጂ ከኢየሩሳሌም አትውጡ፤


“ነገር ግን ከአብ የሚወጣና እኔም ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኙ የእውነት መንፈስ ሲመጣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።


“እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ ወንድሞችና እናንተም እግዚአብሔርን የምትፈሩ አሕዛብ! ይህ የመዳን ቃል የተላከው ለእኛ ነው።


ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”


እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ የሚኖር አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!”


የሕያው አምላክን ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክም ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ ምድርንና ባሕርን እንዲጐዱ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት ድምፁን ከፍ አድርጎ፥


እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን።


ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


እንዲሁም ከሕፃንነትህ ጀምረህ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ትምህርት የሚሰጡህን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዐውቀሃል።


የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያደርስና በሥራውም እንደማያፍር ሠራተኛ ሆነህ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብና ተቀባይነትን ለማግኘት ጥረት አድርግ።


በእርግጥ ስለ እርሱ ሰምታችኋል፤ በኢየሱስ ባለው እውነት መሠረትም ከእርሱ ተምራችኋል።


በእውነት ቃልና በእግዚአብሔር ኀይል ነው። የማጥቂያም ሆነ የመከላከያ መሣሪያችን ጽድቅ ነው፤


የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል ግን እግዚአብሔር እውነተኛ መሆኑን ያረጋግጣል።


ስለዚህ ርኲሰትንና የክፋትንም ብዛት ሁሉ አስወግዳችሁ እግዚአብሔር በልባችሁ የተከለውንና ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios