Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ያዕቆብ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ ምኞት ስትፀንስ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ስታድግ ሞትን ትወልዳለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ምኞት ከፀነሰች በኋላ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

Ver Capítulo Copiar




ያዕቆብ 1:15
21 Referencias Cruzadas  

ኃጢአተኞች በደልን ይፀንሳሉ፤ ተንኰልን ያረግዛሉ፤ ውሸትን ይወልዳሉ።


እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተንኰልን ያቅዳሉ፤ ችግርንም ይወልዳሉ፤ ልባቸውም በአታላይነት የተሞላ ነው።”


ነገር ግን ከእርሱ በበላህበት ቀን በእርግጥ ስለምትሞት ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት ከሚሰጠው ዛፍ ፍሬ አትብላ።”


ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።


ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።


በዚያን ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው አስቀሮታዊው ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆች ሄደና


ክፉዎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ። እግዚአብሔርንም ከረሱ ሕዝቦች ጋር ይቀላቀላሉ።


እርስዋንም ሄደው ያመጡለት ዘንድ ዳዊት መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም ሄደው አመጡለትና ከእርስዋ ጋር ግንኙነት አደረገ፤ በዚህም ጊዜ ሴትዮዋ ወርኃዊ የመንጻት ሥርዓትዋን የፈጸመች ጥብቅ ነበረች፤ ከዚህ በኋላ ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ተመልሳ ሄደች።


መልካም ሥራ ለመሥራት ቊርጥ ውሳኔ ያደረገ ሰው በሕይወት ይኖራል፤ ስሕተት በማድረግ የሚጸና ግን ይሞታል።


ገለባን ፀንሳ እብቅ እንደምትወልድ እስትንፋሳችሁ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያችኋል።


እኔ ግን ‘ሴትን ተመልክቶ የተመኛት ሁሉ፥ ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመነዘረ’ እላችኋለሁ።


ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በገዛ ራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው።


እግዚአብሔር የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios