ዕብራውያን 9:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሁለተኛዋ ውስጠኛ ክፍል የሚገባው ግን የካህናቱ አለቃ ብቻ ነው፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ቀን ብቻ ነው፤ እርሱም ስለ ራሱ ኃጢአትና ሕዝቡ ባለማወቅ ስላደረገው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወደ ውስጠኛው ክፍል የሚገባው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ነበር፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ስለ ራሱ ኀጢአትና ሕዝቡ ባለማወቅ ስላደረገው ኀጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ ከቶ አይገባም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፤ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሁለተኛዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህናቱ ኀጢአታቸውን ለማስተስረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚያቀርበውን ደም ይዞ፥ በየዓመቱ አንድ ጊዜ ብቻውን ይገባ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ |
ምናሴ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከፊታቸው እንዲባረሩ ያደረጋቸው ሕዝቦች ካደረጉት ይበልጥ የከፋ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረጋቸው።”
አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።”
ነቢያቱና ካህናቱ እንኳ ሰክረው ይንገዳገዳሉ፤ ብዙ ወይን ጠጅና የሚያሰክርም ጠንካራ መጠጥ ስለ ጠጡ አእምሮአቸው ታውኮ ይሰናከላሉ፤ ነቢያቱ ሰክረው ከመደናበራቸው የተነሣ እግዚአብሔር የገለጠላቸውን ራእይ አያስተውሉም፤ ካህናቱም እጅግ ስለሚሰክሩ ለሚቀርብላቸው ጉዳይ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት አይችሉም።
አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።”
ገንዘብ አበዳሪዎች ሕዝቤን ያራቊታሉ፤ አራጣ አበዳሪዎችም ይበዘብዙአቸዋል፤ ሕዝቤ ሆይ፥ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጣምማሉ።
ስለዚህ ከእንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቁታል፤ የጥንቈላ ዘንጋቸውም ለጥያቄአቸው መልስ የሚሰጥ ይመስላቸዋል፤ በዝሙት መንፈስም ተመርተው ከእግዚአብሔር ርቀዋል።
በዓመት አንድ ጊዜ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ሁሉ ማስተስረይ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።” በዚህም ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ።
ከመንጋው ምንም ነውር የሌለበት ተባዕት በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ወደ ካህን ያምጣ፤ ዋጋውም ተገምግሞ በይፋ በታወቀው ተመን ይወሰን፤ ካህኑም የእንስሳውን መሥዋዕት ስለዚያ ሰው ያቅርብ፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።
ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበር ያስተስርይላቸው፤ ስሕተቱን የፈጸሙት ባለማወቅ ስለ ሆነና ስለ ኃጢአት ስርየት የሚሆነውንም መሥዋዕትና የእህል ቊርባን አድርገው ለእግዚአብሔር ስላቀረቡ፥ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
እርሱ እንደ ሌሎቹ የካህናት አለቆች በመጀመሪያ ስለ ራሱ ኃጢአት፥ በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ነገር በማያዳግም ሁኔታ ፈጽሞታል።