Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከሁለተኛው መጋረጃ በስተኋላ የምትገኘው ውስጠኛዋ ክፍል “ቅድስተ ቅዱሳን” ትባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሁለተኛው መጋረጃ በስተኋላ ቅድስተ ቅዱሳን የተባለ ክፍል ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከሁለተኛውም መጋረጃ ወዲያ ቅድስተ ቅዱሳን የምትባለው ድንኳን ነበረች፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ በስ​ተ​ኋላ የነ​በ​ረ​ች​ውን የው​ስ​ጠ​ኛ​ዪ​ቱን ድን​ኳን ግን ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ይሉ​አት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከሁለተኛውም መጋረጃ ወዲያ ቅድስተ ቅዱሳን የምትባለው ድንኳን ነበረች፥

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 9:3
15 Referencias Cruzadas  

ቅድስተ ቅዱሳን ተብሎ የሚጠራ አንድ ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፤ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር፤


ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደስ በማግባት በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፍ ሥር አኖሩት።


ለቅድስተ ቅዱሳኑ ከበፍታና ከሌላም ዐይነት ጨርቅ የተሠራ መጋረጃ ተደርጎለት ነበር፤ የመጋረጃውም ቀለም ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ሲሆን በላዩም ላይ የኪሩቤል ምስሎች ተቀርጸውበት ነበር።


ታቦቱንም ወደ ድንኳኑ ውስጥ አስገባውና የሚከለልበትን መጋረጃ ሰቀለ፤ በዚህም ዐይነት ልክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ታቦቱን ሸፈነው።


ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉበትን ጽላት የያዘውን የቃል ኪዳኑን ታቦት በውስጡ አኑር፤ ለመከለያ የተሠራውንም መጋረጃ ከፊት ለፊቱ አድርግ።


በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ ጋርዶ የነበረውን የሐዘን መጋረጃ ያስወግዳል።


ከመካከለኛው ክፍል ባሻገር ያለውን ውስጠኛ ክፍል ከማእዘን እስከ ማእዘን ሲለካ ርዝመቱ ኻያ ክንድ ወርዱም ኻያ ክንድ ሆነ፤ ከዚያም በኋላ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።


“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።


በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ፤ ምድርም ተናወጠች፤ አለቶችም ተሰነጠቁ፤


ይህ ተስፋ ለሕይወታችን እንደማይነቃነቅ አስተማማኝ መልሕቅ ነው፤ በኢየሱስ ያለን ተስፋ መጋረጃውን አልፎ ወደ መቅደስ ይገባል።


ወደ ሁለተኛዋ ውስጠኛ ክፍል የሚገባው ግን የካህናቱ አለቃ ብቻ ነው፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ቀን ብቻ ነው፤ እርሱም ስለ ራሱ ኃጢአትና ሕዝቡ ባለማወቅ ስላደረገው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም።


የመጀመሪያይቱ ድንኳን እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ ገና ያልተገለጠ መሆኑን መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዐይነት ያሳያል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos