ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
ዘፍጥረት 20:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምን “እነሆ የእኔ ግዛት በፊትህ ነው፤ በፈለግከው ስፍራ ኑር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም አብርሃምን፣ “እነሆ፤ አገሬ አገርህ ናት፤ በፈቀድህበት ስፍራ መኖር ትችላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም፦ “እነሆ፥ ምድሬ በፊትህ ናት፥ በወደድኸው ተቀመጥ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም አብርሃምን አለው፥ “እነሆ፥ ምድሬ በፊትህ ናት፤ በወደድኸው ተቀመጥ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም፤ እነሆ ምድሬ በፊትህ ናት፤ በወደድኸው ተቀመጥ አለ። |
ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
በዚህ ዐይነት በአገራችን ላይ ከእኛ ጋር መኖር ትችላላችሁ፤ በፈለጋችሁበት ስፍራ በመዘዋወር እየሠራችሁና እየነገዳችሁ ርስትም ይዛችሁ መኖር ትችላላችሁ።”
ታናሽ ወንድማችሁንም ይዛችሁልኝ ኑ፤ በዚህ ዐይነት ታማኞች ሰዎች መሆናችሁንና ሰላዮችም አለመሆናችሁን አረጋግጣለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ በዚህም አገር ቈይታችሁ እንደ ፈለጋችሁ መነገድ ትችላላችሁ።’ ”
እነሆ፥ መላው የግብጽ ምድር የአንተ ነው፤ ስለዚህ አባትህና ወንድሞችህ ምርጥ በሆነችው በጌሴም ምድር እንዲኖሩ አድርግ። ከእነርሱ መካከል ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።”
እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”