ዘዳግም 18:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከማንኛውም የእስራኤል ከተማ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ቦታ ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል በፍጹም ፈቃድ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ቢመጣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል፥ አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በፍጹም ፈቃድ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚቀመጥባቸው በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከተሞች ከአንዲቱ፥ በፍጹም ልብም ሊያገለግል እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚቀመጥባቸው በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከአገር ደጆች ከአንዲቱ ቢወጣ፥ በፍጹም ፈቃድም እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ |
እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።
በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤ በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።
ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።
መሥዋዕትህን ሁሉ ማቅረብ የሚገባህ ከነገዶችህ መካከል የአንዱ ግዛት በሆነው ክፍል እና እግዚአብሔር በሚመርጠው በአንድ ስፍራ ብቻ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህንም ሆነ ሌላውንም እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ በዚያ ስፍራ ብቻ ትፈጽማለህ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
በዐደራ የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ መንጋውን የምትጠብቁትም በግድ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገው ዐይነት፥ በፈቃደኛነት ይሁን፤ ለገንዘብ በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ይሁን።