ኢዮብ 30:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስጋለብከኝ፥ በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤ በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንሥተህ በነፋስ ላይ አስቀመጥከኝ፥ እንዲያዞረኝም አደረግህ፤ ዐውሎ ነፋሱም ያንገዋልለኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀዘን አኖርኸኝ፥ ከሕይወቴም አራቅኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀመጥኸኝ፥ በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ። |
ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።
የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።
ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋትም እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፍስም ከአውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።