እናገር ዘንድ ተውኝ፥ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
አኔ ስናገር ታገሡኝ፤ ከተናገርሁ በኋላ፣ መሣለቅ ትችላላችሁ።
አንድ ጊዜ ለመናገር ዕድል ስጡኝ፤ ከዚያ በኋላ እንደ ፈለጋችሁ መሳለቅ ትችላላችሁ።
እናገር ዘንድ ዝም በሉ፤ ከተናገርሁ በኋላ ትስቁብኛላችሁና፤
ከንቱ ልፍለፋህ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?
“ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥ የፈለገ ነገር ይምጣብኝ።
ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን?
እነርሱም አፋቸውን ከፈቱብኝ፥ እያላገጡ ጉንጬን ጠፈጠፉኝ፥ በአንድነትም ተሰበሰቡብኝ።
ወዳጆቼ ናቁኝ፥ ዓይኔም በእግዚአብሔር ፊት እንባ ታፈሳለች።
አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥ ዓይኔም ማስቈጣታቸውን ትመለከታለች።
“ስሙ፥ ቃሌን ስሙ፥ ይህም እንደ ማጽናናት ይቆጠርላችሁ።
እነሆ፥ ሁላችሁም አይታችኋል፥ ታዲያ ለምን በከንቱ ትባክናላችሁ?”