ኢዮብ 12:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃንም በሌለበት ጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ያቅበዘብዛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርሃን በሌለበት ጨለማ በዳበሳ ይሄዳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃን አጥተው በጨለማ እንዲደናበሩና እንደ ሰከረም ሰው እንዲንገዳገዱ ያደርጋቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይፍገመገማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ይቅበዘበዛሉ። |
ጌታ ግራ የመጋባት መንፈስ በውስጥዋ አፍሶባታል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት።
እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።
አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።
በእኩለ ቀን ዕውር በዳበሳ እንደሚሄደው ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። ዘወትር ትጨቆናለህ፤ ያለማቋረጥም ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።