Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 59:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤ አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ ጀንበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤ በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዳበሳ እንሄዳለን፤ መንገዳችንንም የምንከታተለው በዳበሳ ነው፤ በድንግዝግዝታ እንዳለን ዐይነት በቀትር እንደናቀፋለን፤ በኀያላን ሰዎችም መካከል እንደ ሞቱ ሰዎች ነን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እንደ ዕው​ሮች ወደ ቅጥሩ ተር​መ​ሰ​መሱ፤ ዐይ​ንም እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ተር​መ​ሰ​መሱ፤ በቀ​ት​ርም ጊዜ በመ​ን​ፈቀ ሌሊት እን​ዳለ ሰው ተሰ​ና​ከሉ፤ እንደ ሙታ​ንም ይጨ​ነ​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዓይን እንደ ሌላቸው ተርመሰመስን፥ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 59:10
16 Referencias Cruzadas  

በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ።


የክፋት መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥ እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።


ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፥ እንዲሰበሩም፥ በወጥመድም እንዲያዙ፥ የጌታ ቃል በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በደንብ ላይ ደንብ፥ በደንብ ላይ ደንብ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።


እርሱም መቅደስ ይሆናል፤ ለሁለቱ የእስራኤል ቤት ግን የሚያደናቅፍ ድንጋይ የሚያሰናክልም ዐለት ይሆንባቸዋል፤ ለኢየሩሳሌም ሕዝብም ወጥመድና አሽክላ ይሆናል።


ከእነርሱ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤ ወጥመድ ይገባሉ፤ ይያዛሉም።”


ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።


ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ።


ኖን። ታውረው በመንገድ ላይ ተቅበዘበዙ፥ ልብሳቸው እንዳይዳሰስ በደም ረክሰዋል።


ልብ እንዲቀልጥ፥ ብዙዎች እንዲሰናከሉ ነው፤ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ የሚገድል ሰይፍ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሎአል፥ እንዲገድልም ተጠቅልሎአል።


“በዚያም ቀን፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ “ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ቀኑም በብርሃን ሳለ ምድሩን አጨልማለሁ።


ስለዚህ ለእናንተ ራእይ የሌለው ሌሊት ይሆንባችኋል፥ የማትጠነቁሉበት ጨለማ ይሆንባችኋል፤ ፀሐይ በነቢያት ላይ ትጠልቅባቸዋለች፥ ቀኑም ይጨልምባቸዋል።


ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።


“በዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዐኖቻቸውን አሳወረ፤ ልባቸውውንም አደነደነ።”


በእኩለ ቀን ዕውር በዳበሳ እንደሚሄደው ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። ዘወትር ትጨቆናለህ፤ ያለማቋረጥም ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይኖራል፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ ጨለማው ዐይኖቹን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos