Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 28:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በእኩለ ቀን ዕውር በዳበሳ እንደሚሄደው ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። ዘወትር ትጨቆናለህ፤ ያለማቋረጥም ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በእኩለ ቀን፣ በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። በየዕለቱ ትጨቈናለህ፤ ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በእኩለ ቀን እንደ ዕውር ትደናበራለህ፤ የምትሄድበትንም መንገድ ማግኘት አትችልም፤ የምትሠራውም ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ዘወትር ጭቈናና ምዝበራ ይደርስብሃል፤ የሚረዳህም ሰው አታገኝም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ዕውር በጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​ዳ​ብስ በቀ​ትር ጊዜ ትዳ​ብ​ሳ​ለህ፤ መን​ገ​ድ​ህም የቀና አይ​ሆ​ንም፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ የተ​ገ​ፋህ፥ የተ​ዘ​ረ​ፍ​ህም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 በቀትርም ጊዜ ዕውር በጨለማ እንደሚርመሰመስ ትርመሰመሳለህ፥ መንገድህም የቀና አይሆንም፤ በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህም ትሆናለህ፥ የሚያድንህም የለም።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:29
26 Referencias Cruzadas  

እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።


በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ።


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ስለዚህም ጌታ በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ ዓመት እንዲገዙ አሳልፎ ሰጣቸው።


በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።


እስራኤላውያንም ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዘሉት።


ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤


እነዚህንም ይዘህ ከእነርሱ ጋር ንጻ፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ ገንዘብ ክፈልላቸው፤ ሁሉም ስለ አንተ የተማሩት ከንቱ እንደ ሆነና አንተ ራስህ ደግሞ ሕጉን እየጠበቅህ በሥርዓት እንድትመላለስ ያውቃሉ።


በሰዎች ላይ ጭንቀትን አመጣለሁ፤ እንደ ዕውርም ይሄዳሉ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፥ ሥጋቸውም እንደ ጉድፍ ይጣላል።


ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፥ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፥


ባርያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም።


ብርሃንም በሌለበት ጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ያቅበዘብዛቸዋል።


ስለ ኃጢአታችንም ለሾምህብን ነገሥታት በረከትዋን ታበዛለች፥ ሰውነታችንንም ይገዛሉ፥ በእንስሶቻችንም የሚወድዱትን ያደርጋሉ፥ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን።”


በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፥ ሰዎቹም ደጃፉን ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ።


ጌታም ሙሴን፦ “በግብጽ ምድር ላይ ጨለማ እንዲሆን፥ ማንም ሰው የሚያውቀው ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማያት ዘርጋ” አለው።


ጌታ በእብደት፥ በዕውርነትና ግራ በማጋባት ይመታሃል።


በጽዮን፦ ‘እንዴት ተበዘበዝን! ምድሪቱንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አብዝተን አፈርን!’ የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።”


ኖን። ታውረው በመንገድ ላይ ተቅበዘበዙ፥ ልብሳቸው እንዳይዳሰስ በደም ረክሰዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios