ሆሴዕ 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአሕዛብ መካከል ወዳጆችን በገንዘብ ቢቀጥሩም እንኳ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ ከንጉሥና ከአለቆችም ሸክም የተነሣ በቶሎ ይመነምናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ በንጉሥና በአለቆች ጭቈና ሥር፣ እየመነመኑ ይሄዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥታትን ለመለማመጥ ዋጋ ቢከፍሉም እንኳ እኔ በአንድነት እሰበስበዋለሁ፤ ነገሥታትና መሳፍንት በሚያደርጉባቸው ጭቈና እየመነመኑ ይሄዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ለአሕዛብ አልፈው ይሰጣሉ፤ እኔም አሁን እቀበላቸዋለሁ፤ ንጉሥንና አለቆችንም ይቀቡ ዘንድ ፈጽመው ያንሣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለአሕዛብ እጅ መንሻ ቢሰጡ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፥ ከንጉሥና ከአለቆችም ሸክም የተነሣ ይደክማሉ። |
ነገር ግን ከጥቂት ዓመቶች በኋላ ንጉሥ ሆሴዕ፥ ሶእ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ግብጽ ንጉሥ መልእክተኞች በመላክ ይረዳው ዘንድ ጠየቀ፤ በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ይሰጠው የነበረውንም ግብር አቆመ፤ ሰልምናሶር ይህን በሰማ ጊዜ ሆሴዕን አስይዞ ወህኒ ቤት አስገባው።
የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌል-ቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ አቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።
ነቢዩንም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “በዐይኖችህ እንደምታየን ከብዙ ጥቂት ተርፈናልና ልመናችን እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ ስለ እኛና ስለዚህ ትሩፍ ሁሉ ለጌታ ለአምላክህ ጸልይ፥
ለአመንዝራዎች ሁሉ ሥጦታ ይሰጡአቸዋል፥ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ሥጦታሽን ትሰጫለሽ፥ ለአመንዝራነትሽ ከየአቅጣጫው ወደ አንቺ እንዲገቡ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ።
ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ።
ሰው ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቆርቆሮንም ለማቅለጥ እሳትን ሊያነድበት በማቅለጫ እንደሚሰበስብ፥ እንዲሁ በቁጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶች፥ ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞች፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
ኤፍሬም ነፋስን ያሰማራል፥ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዓመጻን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።