Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ አል​ፈው ይሰ​ጣሉ፤ እኔም አሁን እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ንጉ​ሥ​ንና አለ​ቆ​ች​ንም ይቀቡ ዘንድ ፈጽ​መው ያን​ሣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ በንጉሥና በአለቆች ጭቈና ሥር፣ እየመነመኑ ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከአሕዛብ መካከል ወዳጆችን በገንዘብ ቢቀጥሩም እንኳ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ ከንጉሥና ከአለቆችም ሸክም የተነሣ በቶሎ ይመነምናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መንግሥታትን ለመለማመጥ ዋጋ ቢከፍሉም እንኳ እኔ በአንድነት እሰበስበዋለሁ፤ ነገሥታትና መሳፍንት በሚያደርጉባቸው ጭቈና እየመነመኑ ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ነገር ግን ለአሕዛብ እጅ መንሻ ቢሰጡ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፥ ከንጉሥና ከአለቆችም ሸክም የተነሣ ይደክማሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 8:10
21 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ እነሆ እኔ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽ​ሞ​ች​ሽን በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ት​ወ​ጃ​ቸ​ው​ንም ከም​ት​ጠ​ያ​ቸው ጋር በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻል፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽን እገ​ል​ጥ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ሁሉም ኀፍ​ረ​ት​ሽን ያዩ​ብ​ሻል።


ስለ ሁለ​ቱም ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ቸው በገ​ሠ​ጻ​ቸው ጊዜ አሕ​ዛብ በላ​ያ​ቸው ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰ​ሜን የነ​ገ​ሥ​ታት ንጉሥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከሰ​ረ​ገ​ሎች፥ ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችም፥ ከጉ​ባ​ኤና ከብዙ ሕዝ​ብም ጋር በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ለሁ።


“አንተ ብቻ​ህን አለቃ ነህን?” ቢሉ​ትም፥ የሔ​ማ​ትን መን​ደር ወሰ​ድሁ ይላል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፣


እን​ዲ​ያ​ቀ​ል​ጡት እሳት ያና​ፉ​በት ዘንድ ብር​ንና መዳ​ብን፥ ብረ​ት​ንና እር​ሳ​ስን፥ ቆር​ቆ​ሮ​ንም በከ​ውር እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስቡ፥ እን​ዲሁ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ውስጥ እጨ​ም​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ አቀ​ል​ጣ​ች​ሁ​ማ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።


ራፋ​ስ​ቂ​ስም ቆሞ በታ​ላቅ ድምፅ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ እን​ዲህ ብሎ ጮኸ፥ “የታ​ላ​ቁን የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ቃል ስሙ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር በእ​ርሱ ላይ ዘመተ፤ ሆሴ​ዕም ተገ​ዛ​ለት፤ ግብ​ርም አመ​ጣ​ለት።


በቍ​ጥር እን​ዳ​ነሱ፥ የታ​ሰ​ረ​ውና የተ​ለ​ቀ​ቀ​ውም እንደ ጠፋ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም የሚ​ረዳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ የመ​ረ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭን​ቀት አየ።


ለአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎች ሁሉ ዋጋ ይሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ አንቺ ግን ለወ​ዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰ​ጫ​ለሽ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ለማ​መ​ን​ዘር በዙ​ሪ​ያሽ ይገ​ቡ​ብሽ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ትሰ​ጫ​ቸ​ዋ​ለሽ።


“ሐላም አመ​ነ​ዘ​ረ​ች​ብኝ፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በሆ​ሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበ​ርና፤ እንደ ልማ​ዱም በየ​ዓ​መቱ ለአ​ሦር ንጉሥ ግብር አል​ሰ​ጠ​ምና፤ ስለ​ዚህ የአ​ሦር ንጉሥ ተዋ​ጋው፤ ይዞም በወ​ህኒ ቤት አሰ​ረው።


እኔን ሳይ​ጠ​ይቁ በፈ​ር​ዖን ኀይል ይረዱ ዘንድ በግ​ብ​ፅም ይጠ​በቁ ዘንድ ወደ ግብፅ ይሄ​ዳሉ።


ኤፍ​ሬም ግን ክብ​ር​ንና ከንቱ ነገ​ርን የሚ​ያ​ሳ​ድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁል​ጊ​ዜም ሐሰ​ት​ንና ተን​ኰ​ልን ያበ​ዛል፤ ከአ​ሦ​ርም ጋር ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋል፤ ምሕ​ረ​ትም ያደ​ር​ጉ​ለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይ​ትን ይል​ካል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios