ሕዝቅኤል 16:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም37 በዚህ ምክንያት ደስ የተሠኘሽባቸውን ወዳጆችሽን፣ የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከየአቅጣጫው ሁሉ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፤ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረተ ሥጋሽን ሁሉ ያያሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር የተደሰትሽባቸውን ማለት የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ ተጋልጠሽ ዕርቃንሽን ያዩ ዘንድ ከአካባቢው ሰብስቤ አንቺን በፊታቸው አራቊትሻለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 ስለዚህ እነሆ እኔ ከአንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ የምትወጃቸውንም ከምትጠያቸው ጋር በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ ይከቡሻል፤ በእነርሱም ዘንድ ጕስቍልናሽን እገልጥብሻለሁ፤ ሁሉም ኀፍረትሽን ያዩብሻል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽ ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፥ በአንቺ ላይ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፥ ኅፍረተ ሥጋሽንም ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ። Ver Capítulo |