ሕዝቅኤል 22:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ሰው ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቆርቆሮንም ለማቅለጥ እሳትን ሊያነድበት በማቅለጫ እንደሚሰበስብ፥ እንዲሁ በቁጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ሰው ብርንና መዳብን፣ ብረትንና እርሳስን እንዲሁም ቈርቈሮን ለማቅለጥ በከውር ውስጥ አስገብቶ እሳት እንደሚያነድድበት፣ እኔም እንደዚሁ በቍጣዬና በመዓቴ ወደ ከተማዪቱ እሰበስባችኋለሁ፤ በዚያም አቀልጣችኋለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ብር፥ መዳብ፥ ብረት፥ እርሳስና ቆርቆሮ ተሰብስበው ወደ ማቅለጫ እንደሚጨመሩና እንዲቀልጡ እሳት ከስር እንደሚነድባቸው እኔም እናንተን በኀይለኛ ቊጣዬ ሰብስቤ እንድትቀልጡ አደርጋለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን፥ ብረትንና እርሳስን፥ ቆርቆሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፤ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ፤ አቀልጣችሁማለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቈርቈሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ። Ver Capítulo |