“እንዲመለሱና በሚግዶልና በባሕሩ መካከል፥ በበዓልጽፎንም ፊት ለፊት ባለው በፒሃሒሮት ፊት እንዲሰፍሩ የእስራኤልን ልጆች ንገራቸው፤ ከእርሱም አንጻር በባህሩ ትሰፍራላችሁ።”
ሕዝቅኤል 29:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ በወንዞችህም ላይ ነኝ፥ የግብጽን ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴቬኔና እስከ ኢትዮጵያ ጠረፍ ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በወንዞችህ ላይ ተነሥቻለሁ፤ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል እስከ አስዋን ከዚያም እስከ ኢትዮጵያ ወሰን ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በአንተና በወንዝህ ላይ በቊጣ ተነሥቻለሁ፤ በሰሜን ከሚግዶል ከተማ አንሥቼ በደቡብ እስከ አስዋን ከተማ ድረስ፥ እንዲያውም እስከ ኢትዮጵያ ጠረፍ ድረስ ግብጽን በሙሉ ምድረ በዳ አድርጌ ባዶዋን አስቀራታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ፥ እነሆ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ በጦርና በቸነፈር ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ። |
“እንዲመለሱና በሚግዶልና በባሕሩ መካከል፥ በበዓልጽፎንም ፊት ለፊት ባለው በፒሃሒሮት ፊት እንዲሰፍሩ የእስራኤልን ልጆች ንገራቸው፤ ከእርሱም አንጻር በባህሩ ትሰፍራላችሁ።”
በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ለእስራኤልም ምድር እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ሰይፌን ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፥ ጻድቁንና ክፉውን ከአንቺ ዘንድ አስወግዳለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፥ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ እንዲሁ ብዙ ሕዝቦችን አስነሣብሻለሁ።
እንዲህም ብለህ ተናገር፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “‘ወንዙ የእኔ ነው እኔ ራሴ ሠርቼዋለሁ’ የምትል፥ በወንዞች መካከል የምትተኛ፥ አንተ ታላቅ ድራጎን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።
ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።