ሕዝቅኤል 23:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፦ በዚያኑ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፥ ሰንበቶቼንም ሽረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፤ በዚያ ቀን ቤተ መቅደሴን አረከሱ፤ ሰንበታቴንም አቃለሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የፈጸሙት በደል ይህ ብቻ አይደለም፤ ቤተ መቅደሴንም በዚያን ጊዜ አርክሰዋል፤ ሰንበቴንም ሽረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ደግሞ አድርገውብኛል፤ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፤ ሰንበታቴንም ሽረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ደግሞ አድርገውብኛል፥ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል ሰንበታቴንም ሽረዋል። |
በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”
ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።
ካህናቶችዋም ሕጌን ጥሰዋል፥ ቅዱሳት ነገሮቼንም አርክሰዋል፤ ቅዱስ በሆነ ነገርና በረከሰ ነገር ላይ ልዩነትን አላደረጉም፥ በርኩስ ነገርና በንጹሕ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም፥ ከሰንበቶቼ ዓይናቸውን ሰወሩ፥ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።
የጌጦቻቸውን ውበት ወደ ትዕቢት ለወጡ፥ የርኩሰታቸውን ምስሎችና አስከፊ ነገሮችን ሰሩባቸው፥ ስለዚህ እኔም ይህንን ለእነርሱ ርኩስ ነገር አደርገዋለሁ።