ሕዝቅኤል 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ መቅደሴን በረከሱ ምስሎችሽና በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ስላጐደፍሽ፣ ፊቴን ከአንቺ እመልሳለሁ፤ በርኅራኄ አልመለከትሽም፤ አልምርሽም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 “ስለዚህ ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ክፋትና ርኲሰት የተሞላበት ነገር ሁሉ በመፈጸም ቤተ መቅደሴን በማርከሳችሁ ምክንያት እኔም ያለ ምሕረት እንድትዋረዱ አደርጋለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ስለዚህ፥ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም። Ver Capítulo |