Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 23:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፤ ከጣዖቶቻቸው ጋር አመንዝረዋል፤ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆቻቸውን እንኳ መብል እንዲሆኑ አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 አመንዝረዋል፤ እጃቸውም በደም ተበክሏልና። ከጣዖቶቻቸው ጋራ አመነዘሩ፤ የወለዱልኝን ልጆቻቸውን እንኳ ለእነርሱ መብል ይሆኑ ዘንድ በእሳት ሠውተውላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ሁለቱም አመንዝሮችና ነፍሰ ገዳዮች ናቸው፤ ያመነዘሩት ከጣዖቶች ጋር ሲሆን፥ የገደሉአቸውም ለእኔ የወለዱአቸውን ልጆች ነው፤ ወንዶች ልጆቼን ለጣዖቶቻቸው ሠውተዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ደምም በእ​ጃ​ቸው አለና፥ ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንም ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ ለእ​ኔም የወ​ለ​ዱ​አ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን መብል እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው በእ​ሳት አሳ​ል​ፈ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፥ ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን መብል እንዲሆኑላቸው በእሳት አሳልፈዋቸዋልና።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 23:37
30 Referencias Cruzadas  

ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ።


የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ።


ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤


በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


ይሁዳን ኃጢአት ለማሠራት፥ ይህን ርኩሰት እንዲያደርጉ ባላዛቸውም በልቤም ባላስበውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሌክ በእሳት ለመሠዋት፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።


እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያሉትን የቶፌት መስገጃዎችን ሠረተዋል።


መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትጨቊኑ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም እንዳይሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥


ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤


በባሏ ፋንታ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሴት ሆነሻል።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍትወትሽ ስለ ፈሰሰ፥ ከወዳጆችሽ ጋር ባደረግሽው ዝሙት ዕርቃንሽ ስለ ተገለጠ፥ ስለ ርኩሰትሽም ጣዖታት ሁሉና ለእነርሱ ስለ ሰጠሻቸው ልጆች ደም፥


በአመንዝሮችና በደም አፍሳሽ ሴቶች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፥ የመዓትንና የቅንዓትን ደም አመጣብሻለሁ።


አንቺ ባሏንና ልጆችዋን የጠላች የእናትሽ ልጅ ነሽ፥ አንቺም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የጠሉ የእኅቶችሽ እኅት ነሽ፥ እናታችሁ ኬጢያዊት ነበረች አባታችሁም አሞራዊ ነበረ።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ፥ ማኅፀን የሚከፍተውን ሁሉ በእሳት ባሳለፉ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።


ቁርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤


ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ፥ በዚያው ቀን ሊያረክሱት ወደ መቅደሴ ገብተዋልና፤ እነሆም በቤቴ ውስጥ ይህን አደረጉ።


ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል፤ ምክንያቱም አመንዝሮች ናቸውና፥ ደምም በእጃቸው አለና።


ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው።


ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ ጌታ እንደሚወድዳቸው እንዲሁ አንተም ዳግመኛ ሂድ፥ በውሽማዋ የምትወደደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ።”


መራገምና መዋሸት፥ መግደልና መስረቅ፥ ማመንዘርም ገደባቸውን አልፈዋል፤ ደም ማፍሰስ ደም ማፍሰስን አስከትሏል።


ከልጆችህ ማናቸውንም ለሞሌክ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ አትስጥ፥ በዚህም የአምላክህን ስም አታርክስ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ።


ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።


አምላክህን ጌታ በእነርሱ መንገድ ፈጽሞ አታምልክ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን ሲያመልኩ ጌታ የሚጸየፈውን ሁሉንም ዓይነት ነገር ያደርጋሉና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እንኳን ለአማልክታቸው መሥዋዕት አድርገው ያቃጥላሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos