ሕዝቅኤል 20:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 “ ‘ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ ዐመፀብኝ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልጠበቁም፤ ሕጌንም ተላለፉ፤ ሰንበቴንም ፈጽሞ አረከሱ። እኔም መዓቴን ላፈስስባቸው፣ በምድረ በዳም ላጠፋቸው ወስኜ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ነገር ግን የእስራኤልን ቤት በምድረ በዳ በትእዛዜ ሂዱ አልኋቸው፤ አልሄዱምም፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ሕጌን አፈረሱ፤ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፥ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ። Ver Capítulo |