ሕዝቅኤል 20:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና ወደ ደቡብም ተናገር በደቡብም ባለው ዱር ላይ ትንቢት ተናገር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ደቡብ አዙር፤ በደቡብ ላይ ቃል ተናገር፤ በደቡብ አገር ደን ላይም ትንቢት ተንብይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! ወደ ደቡብ ፊትህን አዙረህ በደቡብ ላይ ተናገር፤ በደቡብ በኩል ባለው ጫካ ላይም ትንቢት ተናገርበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ቴማን አቅና፤ ወደ ዳሮምም ተመልከት፤ በናጌብም ምድረ በዳ ዱር ንጉሥ ላይ ትንቢት ተናገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና ወደ ደቡብም ተናገር በደቡብም ባለው ዱር ላይ ትንቢት ተናገር፥ |
በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥