ዘፀአት 23:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርህ የምትጨነግፍ ወይም መካን አትኖርም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድርህም የሚያስወርዳት ወይም መካን ሴት አትኖርም፤ ረዥም ዕድሜም እሰጥሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድርህ ፅንስ የሚያስወርዳት ወይም መኻን ሴት አትኖርም፤ ዕድሜህንም አረዝመዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርህም መካን፥ ወይም የማይወልድ አይኖርም፤ የዘመንህንም ቍጥር እሞላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ። |
ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ የመቶ ዓመት ሳይሆነው የሚሞት እንደተረገመ ኃጢአተኛ ይታያል።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”