Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የቀ​ደሙ አባ​ቶች ውዳሴ

1 የከ​በሩ ሰዎ​ች​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በዘ​መ​ና​ቸው እና​መ​ስ​ግ​ና​ቸው።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዙ ክብ​ርን ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ ከመ​ጀ​መ​ሪያ ጀምሮ አግ​ን​ኖ​አ​ቸ​ዋ​ልና።

3 በኀ​ይ​ላ​ቸው ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ፥ በጥ​በ​ባ​ቸው የሚ​መ​ክሩ፥ ትን​ቢ​ት​ንም የሚ​ና​ገሩ ሰዎች በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸው ገዙ።

4 የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት በሰ​ል​ፋ​ቸው፥ የሕ​ዝ​ቡም ጸሓ​ፊ​ዎች በም​ክ​ራ​ቸው፥ በል​ባ​ቸ​ውም ባለ በቃ​ላ​ቸው ጥበብ፤

5 ምስ​ጋ​ና​ንና ያማረ መሰ​ን​ቆን የሚ​ፈ​ልጉ፥ በመ​ጽ​ሐፍ እንደ ተጻፈ አድ​ር​ገው የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ፥

6 ባለ​ጸ​ጎች የሆኑ ገን​ዘ​ባ​ቸው የሚ​በ​ቃ​ቸው፥ በቤ​ታ​ቸው በደ​ኅና የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም፤

7 እነ​ዚህ ሁሉ በዘ​መ​ና​ቸው የከ​በሩ፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውም የተ​ዘ​ጋጁ ናቸው፤

8 ከእ​ነ​ር​ሱም ውዳ​ሴ​ያ​ቸው ይነ​ገር ዘንድ፥ የከ​በረ ስምን የተዉ አሉ።

9 የሚ​ያ​ስ​ባ​ቸው የሌለ፥ የጠ​ፉም፥ እን​ዳ​ል​ተ​ፈ​ጠ​ሩና እን​ዳ​ል​ተ​ወ​ለዱ የሆ​ኑም አሉ። ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋራ እንደ እነ​ርሱ ጠፉ።

10 እነ​ዚህ ግን ጽድ​ቃ​ቸው ያል​ተ​ዘ​ነ​ጋ​ች​ባ​ቸው፥ ይቅ​ር​ታን የተ​ሞሉ ናቸው፤

11 ያማ​ረች ርስ​ታ​ቸ​ውም ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋራ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንታ ትኖ​ራ​ለች። ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ይኖ​ራሉ።

12 ዘራ​ቸው ፈጥኖ ይቆ​ማል፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ናቸው፤

13 ዘራ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ክብ​ራ​ቸ​ውም አያ​ል​ቅም።

14 ሥጋ​ቸ​ውም በሰ​ላም ተቀ​በረ፤ ስማ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንታ ትኖ​ራ​ለች።

15 አሕ​ዛ​ብም ጥበ​ባ​ቸ​ውን ይና​ገ​ራሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሸንጎ ያመ​ሰ​ግ​ኗ​ቸ​ዋል።


ስለ ሄኖ​ክና ኖኅ

16 ሄኖክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ሱን ሰወ​ረው፤ ንስ​ሓም ይገቡ ዘንድ ለት​ው​ልድ ሁሉ አብ​ነት ሆነ።

17 ኖኅም ፍጹ​ምና ጻድቅ ሆኖ ተገኘ፤ በጥ​ፋ​ትም ዘመን እርሱ ለዓ​ለም ምክ​ን​ያት ሆነ፤ የጥ​ፋ​ትም ውኃ በወ​ረደ ጊዜ እርሱ ለም​ድር ዘር ሆኖ ቀረ።

18 የጥ​ፋት ውኃ ሰውን ሁሉ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


ስለ አብ​ር​ሃም

19 የአ​ሕ​ዛብ ሁሉ አባት አብ​ር​ሃም ታላቅ ነው፤ የል​ዑ​ልን ሕግ የጠ​በቀ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን ያደ​ረገ፥ በክ​ብር እር​ሱን የሚ​መ​ስል አል​ተ​ገ​ኘም።

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ው​ነቱ ቃል ኪዳ​ንን አጸ​ና​ለት። በፈ​ተ​ነ​ውም ጊዜ የታ​መነ ሆኖ ተገኘ።

21 ስለ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ በዘሩ ይባ​ረኩ ዘንድ፥ እንደ ባሕር አሸ​ዋም ያበ​ዛ​ቸው ዘንድ፥ ዘሩም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት ይበዙ ዘንድ፥ ከባ​ሕር እስከ ባሕ​ርም ድረስ ያወ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ከወ​ን​ዞ​ችም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያወ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ቃል ኪዳ​ንን አጸ​ና​ለት፥


ይስ​ሐ​ቅና ያዕ​ቆብ

22 ለይ​ስ​ሐ​ቅም ስለ አባቱ ስለ አብ​ር​ሃም ደግ​ነት፥ ለሰው ሁሉ የም​ት​ሆን በረ​ከ​ት​ንና ቃል ኪዳ​ንን አጸ​ና​ለት።

23 በያ​ዕ​ቆብ ራስ ላይም ዐረ​ፈች፥ በረ​ከ​ቱም ተገ​ለ​ጠ​ች​ለት፥ እር​ሷ​ንም ርስት አድ​ርጎ ሰጠው፤ ርስ​ታ​ቸ​ው​ንም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ለየ​ላ​ቸው፥ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ነገ​ድም ርስ​ታ​ቸ​ውን ከፈ​ለ​ላ​ቸው።

24 ከእ​ነ​ር​ሱም የከ​በ​ሩና በሰው ዘንድ ሞገ​ስን ያገኙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ዘን​ድም የተ​ወ​ደዱ ጻድ​ቃን ሰዎ​ችን አስ​ነሣ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች