የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ካልእ 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ካልእ 5

1 እር​ሱም ታና​ናሽ ልጆ​ቹን ትቶ ሞተ፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ሥር​ዐት እንደ ሠራ​ላ​ቸው አደጉ፤ የቤ​ታ​ቸ​ው​ንም ሥር​ዐት ጠበቁ፤ ወገ​ና​ቸ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብቁ ነበር፤ ድሃ​ው​ንና ባል​ቴ​ቶ​ችን፥ የሙት ልጆ​ች​ንም አያ​ስ​ጮ​ሁም ነበር።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈ​ሩት ነበር፤ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ለድ​ሆች ይመ​ጸ​ውቱ ነበር፤ አባ​ታ​ቸ​ውም አደራ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ ይጠ​ብቁ ነበር፤ ባል​ቴ​ት​ዋ​ንና የሙት ልጆ​ች​ንም በች​ጋ​ራ​ቸው ጊዜ ያረ​ጋ​ጓ​ቸው ነበር፤ አባ​ትና እና​ትም ይሆ​ኗ​ቸው ነበር፤ ከሚ​በ​ድ​ሏ​ቸው ሰዎች እጅ ያስ​ጥ​ሏ​ቸው፥ ካገ​ኛ​ቸው ሁከ​ትና ኀዘ​ንም ሁሉ ያረ​ጋ​ጓ​ቸው ነበር።

3 እን​ዲ​ህም እያ​ደ​ረጉ አም​ስት ዓመት ኖሩ።

4 ከዚ​ህም በኋላ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ንጉሥ ጺሩ​ጻ​ይ​ዳን መጣ፤ ሀገ​ራ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አጠፋ፤ የመ​ቃ​ቢ​ስ​ንም ልጆች ማረ​ካ​ቸው፤ መን​ደ​ራ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አጠፋ።

5 ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ዘረፈ፤ እነ​ር​ሱ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛ​ዝና ፍርድ የማ​ይ​ሔዱ፥ ነገር ግን በክ​ፋት ሁሉና በዝ​ሙት፥ በር​ኵ​ሰ​ትና በስ​ስት፥ በፅ​ር​ፈ​ትና አም​ላ​ካ​ቸ​ውን ባለ​ማ​ሰብ የሚ​ሔዱ ጣዖት አም​ላ​ኪ​ዎች ይዘው ወደ ሀገ​ራ​ቸው ወሰ​ዷ​ቸው።

6 የሞ​ተ​ው​ንና ደሙን፥ አውሬ የበ​ላ​ው​ንና የበ​ከ​ተ​ውን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የማ​ይ​ወ​ድ​ደ​ውን ሁሉ ይበ​ላሉ፤ በኦ​ሪት ከተ​ጻ​ፈው ከእ​ው​ነ​ተ​ኛው ትእ​ዛ​ዝም ሁሉ ሕግ የላ​ቸ​ውም።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ከእ​ና​ታ​ቸው ማኅ​ፀን ያወ​ጣ​ቸ​ውና በሚ​ገባ የመ​ገ​ባ​ቸው፥ ፈጣ​ሪ​ያ​ቸ​ውና መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸ​ውም እንደ ሆነ አያ​ው​ቁ​ትም።

8 በፍ​ርድ ጊዜም ሕግ የላ​ቸ​ውም፤ የእ​ን​ጀራ እና​ታ​ቸ​ው​ንና አክ​ስ​ታ​ቸ​ውን አግ​ብ​ተው ወደ ቅሚ​ያና ወደ ክፉ ነገር፥ ወደ ኀጢ​አ​ትና ወደ ዝሙ​ትም ይሄ​ዳሉ እንጂ። ክፉ​ው​ንም ሁሉ ያደ​ር​ጋሉ፤ እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዘመ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያገ​ባሉ፤ ሕግም የላ​ቸ​ውም።

9 መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ሁሉ ድጥና ጨለማ፤ ርኵ​ሰ​ትና ዝሙት ነው።

10 እነ​ዚያ የመ​ቃ​ቢስ ልጆች ግን በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሁሉ ይጠ​በቁ ነበር፤ ሞቶ ያደ​ረ​ው​ንና አባላ የተ​መ​ታ​ውን አይ​በ​ሉም ነበር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ልጆች ርኵ​ሰ​ትና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ አይ​ሠ​ሩም ነበር። በዚህ መጽ​ሐፍ ያል​ተ​ጻፈ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የወ​ን​ጀ​ለ​ኞች፥ የመ​ና​ፍ​ቃ​ንና የከ​ዳ​ተ​ኞች፥ ፍጹም ርኩ​ሰ​ት​ንና ቅሚ​ያን የተ​ሞሉ የአ​ረ​ማ​ው​ያን ልጆች የሚ​ሠ​ሩት ሥራ​ቸው ክፉና ብዙ ነበ​ርና።

11 ፈጣ​ሪ​ያ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ድ​ደው ሥራ ሁሉ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ አል​ነ​በ​ረም።

12 ዳግ​መ​ኛም ስሙ ብኤል ፌጎር የሚ​ባል ጣዖ​ትን ያመ​ልኩ ነበር፤ እንደ ፈጣ​ሪ​ያ​ቸው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያመ​ል​ኩ​ትና ይታ​መ​ኑት ነበር። እርሱ ግን ደን​ቆ​ሮና ዲዳ ስለ​ሆነ የሚ​ያ​የ​ውና የሚ​ሰ​ማው የለም፤ የሰው እጅ ሥራ ጣዖት ነውና፤ ብርና ወር​ቅን የሚ​ሠራ አን​ጥ​ረኛ የሠ​ራው፥ ትን​ፋ​ሽና ዕው​ቀት የሌ​ለው የሰው እጅ ሥራ ነው፤

13 አይ​በ​ላም፤ አይ​ጠ​ጣ​ምም።

14 አይ​ገ​ድ​ልም፦ አያ​ድ​ን​ምም።

15 አይ​ተ​ክ​ልም፦ አይ​ነ​ቅ​ል​ምም።

16 መል​ካም አያ​ደ​ር​ግም፤ ክፉም አያ​ደ​ር​ግም።

17 አያ​ደ​ኸ​ይም፦ አያ​ከ​ብ​ር​ምም።

18 አይ​ቀ​ሥ​ፍም፤ ይቅ​ርም አይ​ልም። ነገር ግን ሰነ​ፎች የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሕዝብ ለማ​ሳት ዕን​ቅ​ፋ​ትን ይሆ​ናል።