የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ካልእ 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ካልእ 2

1 ረአይ የሚ​ሉት ነቢይ እን​ዲህ አለው፥ “በጊ​ዜው ብር​ሃን ዛሬ ጥቂት ደስ ይበ​ልህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ኸው መቅ​ሠ​ፍት ይበ​ቀ​ልህ ዘንድ አለው።

2 ፈረ​ሶች ፈጣ​ኖች ናቸው፤ ስለ​ዚ​ህም በሩጫ አመ​ል​ጣ​ለሁ ትላ​ለ​ህን?

3 እኔስ የሚ​ከ​ተ​ሉህ ሰዎች ከአ​ሞ​ሮች ይፈ​ጥ​ናሉ፤ ከጥ​ፋ​ትና ከሚ​መ​ጣ​ብህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ አታ​መ​ል​ጥም እል​ሃ​ለሁ።

4 የብ​ረት ልብስ እለ​ብ​ሳ​ለሁ፤ የጦር መወ​ር​ወ​ርና የቀ​ስ​ትም መን​ደፍ አይ​ች​ለ​ኝም ትላ​ለ​ህን? የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​በ​ቀ​ልህ በጦር መወ​ር​ወር አይ​ደ​ለም ይላል፤ ነገር ግን ከጦር መወ​ር​ወ​ርና ከቀ​ስት ንድ​ፈት የሚ​ከፋ ጽኑ የልብ በሽ​ታን፥ እከ​ክ​ንና ቍር​ጥ​ማ​ትን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤

5 ቍጣ​ዬን አነ​ሣ​ሥ​ተ​ሃ​ልና፥ የልብ በሽ​ታን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሚ​ረ​ዳ​ህም ታጣ​ለህ፤ ስም አጠ​ራ​ር​ህ​ንም ከም​ድር እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ ከእጄ አታ​መ​ል​ጥም።

6 አን​ገ​ት​ህን አደ​ን​ድ​ነ​ሃ​ልና ራስ​ህ​ንም በከ​ተ​ማዬ ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ይህን ነገር እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኜ ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ እኔ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቀ​ኛ​ለህ፤ አንተ በፊቴ እሳት እን​ደ​ሚ​በ​ላው በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ ሣር ነህና፥ ዓውሎ ነፋ​ስም ከም​ድር አፍሶ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው ትቢያ ነህና አንተ በእኔ ዘንድ እን​ዲሁ ነህ።

7 ቍጣ​ዬን አነ​ሣ​ሥ​ተ​ሃ​ልና፥ ፈጣ​ሪ​ህ​ንም አላ​ወ​ቅ​ህ​ምና እኔም የአ​ንተ የሆ​ነ​ውን ሁሉ ቸል እለ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ን​ባ​ህም ሁሉ ላይ የሚ​ጠ​ጋ​ውን አላ​ስ​ቀ​ርም።

8 አሁ​ንም ከሠ​ራ​ኸው ክፋት ሁሉ ተመ​ለስ፤ ብት​መ​ለስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ፈጽ​መህ በል​ቅ​ሶና በኀ​ዘን ብት​ና​ዘዝ፥ በን​ጹሕ ልቡ​ናም ወደ እርሱ ብት​ለ​ምን በፊቱ የሠ​ራ​ኸ​ውን ኀጢ​አ​ት​ህን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይል​ሃል።”

9 የዚ​ያን ጊዜም መቃ​ቢስ ትቢያ ለብሶ ስለ ኀጢ​አቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አለ​ቀሰ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​ታ​ልና።

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢዩ ቃል የተ​ና​ገ​ረ​ውን መቅ​ሠ​ፍት እን​ደ​ማ​ያ​ዘ​ገይ ዐወቀ። ዐይ​ኖቹ የተ​ገ​ለጡ ናቸ​ውና አይ​ተ​ኛም፤ ዦሮ​ውም የተ​ከ​ፈተ ነውና ቸል አይ​ልም፤ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም ቃል ሐሰት አያ​ደ​ር​ግ​ምና በአ​ን​ዲት ጊዜ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ያደ​ር​ጋ​ታል።

11 ልብ​ሱ​ንም ጥሎ ማቅ ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሰ፤ ስለ ሠራ​ውም ክፋት በፈ​ጣ​ሪው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጮኸ፤ አለ​ቀ​ሰም።