የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 101:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከጩ​ኸቴ ድምፅ የተ​ነሣ ሥጋዬ በአ​ጥ​ን​ቶቼ ላይ ተጣ​በቀ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣ አጠፋዋለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣ እርሱን አልታገሠውም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 101:5
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕው​ቀ​ትህ በእኔ ላይ ተደ​ነ​ቀች፤ በረ​ታ​ች​ብኝ፥ ወደ እር​ሷም ለመ​ድ​ረስ አል​ች​ልም።


ፈቃ​ድህ ሁሉ በም​ድር ባሉት ቅዱ​ሳን ላይ ተገ​ለጠ።


“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ላይ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር።


“ሐሰ​ተኛ ወሬ አት​ቀ​በል፤ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ርም ትሆን ዘንድ ከዐ​መ​ፀኛ ጋር አት​ቀ​መጥ።


ልዝብ ከንፈሮች ጥልን ይሸፍናሉ፤ ስድብን የሚያወጡ ግን ሰነፎች ናቸው።


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፤ በከንፈሩ የሚያባብል ሰውን አትገናኘው።


ለስድብ በልብ አለመቸኮል ታላቅ ዕውቀት ነው የኃጥኣንም ብርሃናቸው ኀጢአት ነው።


የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ሰዎች ዐይ​ኖች ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የሰ​ዎ​ችም ኵራት ትወ​ድ​ቃ​ለች፥ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።


በው​ስ​ጥሽ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአ​ንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአ​ንቺ ውስጥ በተ​ራ​ሮች ላይ በሉ፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም የማ​ይ​ገባ ነገ​ርን አደ​ረጉ።


በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል በሸ​ን​ጋ​ይ​ነት አት​ዙር፤ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም ደም ላይ አት​ቁም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


አሁ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ዘማዊ፥ ወይም ገን​ዘ​ብን የሚ​መኝ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ፥ ወይም ዐመ​ፀኛ፥ ወይም ተራ​ጋሚ፥ ወይም ሰካ​ራም፥ ወይም የሚ​ቀማ ቢኖር እን​ደ​ዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ካለው ሰው ጋር መብ​ልም እንኳ አት​ብሉ፤


እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።


እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤


አት​መኩ፤ የኵ​ራት ነገ​ሮ​ች​ንም አት​ና​ገሩ፤ ፅኑዕ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዙፋ​ኑን ያዘ​ጋ​ጃል።