Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

1 ቆሮንቶስ 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የማ​ይ​ገባ ሥራ በሚ​ሠሩ ላይ የሚ​ሰጥ ቅጣት

1 በእ​ና​ንተ ላይ ዝሙት ይሰ​ማል፤ እን​ደ​ዚህ ያለው ዝሙ​ትም አረ​ማ​ው​ያን እንኳ የማ​ያ​ደ​ር​ጉት ነው፤ ያባ​ቱን ሚስት ያገባ አለና።

2 እና​ን​ተም ከዚህ ጋር ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ናችሁ፤ ይል​ቁ​ንም ይህን ያደ​ረ​ገው ከእ​ና​ንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላ​ዘ​ና​ች​ሁ​በ​ትም?

3 እኔ በሥ​ጋዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ባል​ኖር፥ በመ​ን​ፈሴ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠ​ራ​ውን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ።

4 በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ፥ በእኔ ሥል​ጣን፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ኀይል፥

5 ሥጋ​ውን ጎድቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ለሰ​ይ​ጣን አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡት።

6 እን​ግ​ዲ​ያስ መታ​በ​ያ​ችሁ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጥቂቱ እርሾ ብዙ​ውን ሊጥ እን​ደ​ሚ​ያ​መጥ አታ​ው​ቁ​ምን?

7 እን​ግ​ዲህ ለአ​ዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮ​ጌ​ውን እርሾ ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናች​ሁና፤ ፋሲ​ካ​ችን ክር​ስ​ቶስ ተሠ​ውቶ የለ​ምን?

8 አሁ​ንም በዓ​ላ​ች​ሁን አድ​ርጉ፤ ነገር ግን እው​ነ​ትና ንጽ​ሕና ባለው እርሾ ነው እንጂ በአ​ሮ​ጌው እርሾ፥ በኀ​ጢ​አ​ትና በክ​ፋት እር​ሾም አይ​ደ​ለም።

9 ከዘ​ማ​ው​ያን ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ በዚህ መል​እ​ክት ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።

10 የዚህ ዓለም ዝሙት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ቀማ​ኞ​ችና ዘራ​ፊ​ዎች፥ ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልኩ ደግሞ አሉ፤ ያለ​ዚ​ያስ ከዚህ ዓለም ልት​ለዩ ይገ​ባል።

11 አሁ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ዘማዊ፥ ወይም ገን​ዘ​ብን የሚ​መኝ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ፥ ወይም ዐመ​ፀኛ፥ ወይም ተራ​ጋሚ፥ ወይም ሰካ​ራም፥ ወይም የሚ​ቀማ ቢኖር እን​ደ​ዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ካለው ሰው ጋር መብ​ልም እንኳ አት​ብሉ፤

12 ምን አግ​ዶኝ፥ በውጭ ባለው ላይ እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ? እና​ን​ተስ በው​ስጥ ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ፈር​ዳ​ችሁ ቅጡ​አ​ቸው።

13 በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች