Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 101 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ባዘ​ነና ልመ​ና​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባፈ​ሰሰ ጊዜ የባ​ሕ​ታዊ ጸሎት።

1 አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ጩኸ​ቴም ወደ ፊትህ ይድ​ረስ።

2 በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።

3 ዘመኔ እንደ ጢስ አል​ቋ​ልና፥ አጥ​ን​ቶቼም እንደ ሣር ደር​ቀ​ዋ​ልና።

4 ተቀ​ሠ​ፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። እህል መብ​ላት ተረ​ስ​ቶ​ኛ​ልና

5 ከጩ​ኸቴ ድምፅ የተ​ነሣ ሥጋዬ በአ​ጥ​ን​ቶቼ ላይ ተጣ​በቀ።

6 እንደ ሜዳ አህያ ሆንኹ፤ ሌሊት በወና ቤት እን​ዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ።

7 ተጋሁ፥ በሰ​ገ​ነ​ትም እን​ደ​ሚ​ኖር ብቸኛ ድን​ቢጥ ሆንሁ።

8 ጠላ​ቶቼ ሁል​ጊዜ ይሰ​ድ​ቡ​ኛል፥ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም ተማ​ማ​ሉ​ብኝ።

9 አመ​ድን እንደ እህል ቅሜ​አ​ለ​ሁና፥ መጠ​ጤ​ንም ከእ​ን​ባዬ ጋር ጠጥ​ቻ​ለ​ሁና፥

10 ከቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍት የተ​ነሣ፥ አን​ስ​ተኽ ጥለ​ኸ​ኛ​ልና።

11 ዘመ​ኔም እንደ ጥላ አለፈ፤ እኔም እንደ ሣር ደር​ቄ​አ​ለሁ።

12 አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፥ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ህም ለልጅ ልጅ ነው።

13 አንተ ተነሥ፥ ጽዮ​ን​ንም ይቅር በላት፥ ይቅር ትላት ዘንድ ጊዜዋ ነውና፥ ዘመ​ን​ዋም ደር​ሶ​አ​ልና፤

14 ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ድን​ጋ​ዮ​ች​ዋን ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ መሬ​ቷ​ንም አክ​ብ​ረ​ው​ታ​ልና።

15 አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ስም​ህን፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ ክብ​ር​ህን ይፍሩ፤

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን ይሠ​ራ​ታ​ልና፥ በክ​ብ​ሩም ይገ​ለ​ጣ​ልና።

17 ወደ ድሆች ጸሎት ተመ​ለ​ከተ፥ ልመ​ና​ቸ​ው​ንም አል​ና​ቀም፥

18 ይህ​ችም ለሚ​መጣ ትው​ልድ ተጻ​ፈች፥ የሚ​ፈ​ጠ​ርም ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤

19 ከሰ​ማይ ሆኖ መቅ​ደ​ሱን ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ ምድ​ርን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤

20 የእ​ስ​ረ​ኞ​ችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ የተ​ገ​ደ​ሉ​ት​ንም ሰዎች ልጆች ያድን ዘንድ፤

21 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በጽ​ዮን ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይነ​ግሩ ዘንድ፤

22 አሕ​ዛብ በአ​ን​ድ​ነት በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ ነገ​ሥ​ታ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገዙ ዘንድ።

23 በኀ​ይሉ ጎዳና መለ​ሳ​ቸው፥ የዘ​መ​ኔን ማነስ ንገ​ረኝ።

24 በዘ​መኔ አኩ​ሌታ አት​ው​ሰ​ደኝ፤ ዓመ​ቶ​ችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።

25 አቤቱ፥ አንተ አስ​ቀ​ድ​መህ ምድ​ርን መሠ​ረ​ትህ፥ ሰማ​ያ​ትም የእ​ጅህ ሥራ ናቸው።

26 እነ​ርሱ ይጠ​ፋሉ፥ አንተ ግን ትኖ​ራ​ለህ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረ​ጃል፥ እንደ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ትለ​ው​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይለ​ወ​ጡ​ማል፤

27 አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመ​ት​ህም ከቶ አያ​ል​ቅም።

28 የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ልጆች ይኖ​ራሉ፥ ዘራ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች