Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 101 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


ንጉሥ ለእግዚአብሔር የሚገባው ቃል ኪዳን

1 እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ እዘምራለሁ፤ አዜማለሁም።

2 ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? ከቤተሰቤ ጋር በቅንነት እኖራለሁ።

3 ክፉ ነገር ሲደረግ አይቼ ዝም አልልም፤ ከእግዚአብሔር የራቁ ሰዎች የሚያደርጉትን ሁሉ እጠላለሁ፤ ከቶም አልተባበራቸውም።

4 ጠማማ ልብ ያላቸው ሰዎች ከእኔ ይራቁ፤ ከክፋትም ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም።

5 ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም።

6 ለእግዚአብሔር ታማኞች የሆኑትን እመርጣለሁ፤ አገልጋዮቼም በሕይወታቸው ነቀፋ የሌለባቸው ይሆናሉ።

7 አታላይ ሰው በቤቴና ሐሰትን የሚናገር በእኔ ዘንድ አይኖርም።

8 በምድሪቱ የሚገኙትን ክፉዎች ሰዎች በየዕለቱ ጸጥ አሰኛለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ከተማ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ አጠፋለሁ።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች