Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ጥበብ 14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንደዚሁም ደግሞ ሞገደኛዉን የባሕር ማዕበል በመርከብ ለመሻገር የሚዘጋጅ ሰው፥ እርሱን ከተሸከመችው መርከብ እጅጉን ላነሰ የእንጨት ቁራጭ ልመናዉን ያቀርባል፤

2 የእርሷ ግንባታ የመርከብ ሠራተኛውን ጥበብ ጠይቋል።

3 እርሷን የሚመራት ግን፥ አባት ሆይ፥ ያንተ ጥበቃ ነው፤ አንተ በባሕር ውስጥ መንገድ፥ በማዕበሎችም መካከል መውጫ አበጅተሃል።

4 ማንኛውም ዓይነት አደጋ ቢደርስ፥ አንተ ልታድነው እንደምትችል አሳይተሃልና፥ ልምድ የሌለው ሰው እንኳ በባሕር ላይ ሊጓዝ ይችላል።

5 አንተ የጥበብህ ፍሬዎች እንዲባክኑ አትሻም፤ ከዚህም የተነሣ ሰዎች በትንሿ የእንጨት ስባሪ ተማምነው ማዕበሉን በታንኳ ያቋርጣሉ፤ እንዲያም ሆኖ ግን ካሰቡበት በደኀና ይደርሳሉ።

6 ትዕቢተኞቹ ግዙፋን በጠፉበት በጥንት ዘመን፥ የዓለም ተስፋ በመርከብ ተጠለለ፤ በእጅህም እየተመራ የአዲሱን ትውልድ ዘር ለመጪው ዘመን አቆየ።

7 የጽድቅ መሣሪያ የሆነው እንጨት የተባረከ ነው፤

8 ሰው ሠራሹ ጣኦትና ቀራጩ ግን የተረገሙ ናቸው፤ ቀራጩ ጣኦትን በመሥራቱ፥ ጣኦቱ በስባሽ ቢሆንም እንኳ፥ አምላክ ተብሎ በመጠራቱ ርጉማን ናቸው፤

9 እግዚአብሔር ክፉዎችንና ክፋትን እኩል ይጠላልና፤

10 ሠራተኛውና ሥራው አንድ ዓይነት ቅጣትን ያገኛሉ።

11 በእግዚአብሔር ፍጥረት ውስጥ አስጸያፊ፥ ለሰዎች ነፍስ ሐፍረት፥ ማስተዋል ለጐደላቸው ሰዎች እግሮችም ወጥመድ ሆነዋልና፥ ከዚህም የተነሣ የአሕዛብ ጣኦቶች እንኳን መጎብኘታቸው የማይቀር ነው።


የአምልኮተ ጣኣት አጀማመር

12 ጣኦቶችን የመሥራት ሐሳብ የሴሰኝነት መጀመሪያ፥ የእነርሱም መታወቅ የሕይወት መጥፊያ ሆነ።

13 በቀደመው ዘመን አልነበሩም፤ ዘላለማዊም አይደሉም።

14 የሰው ግብዝነት እነርሱን ወደ ዓለም አመጣቸው፤ የተወሰነላቸውም አጭር ዕድሜ ነው።

15 ያለ ዕድሜው በተቀጨ ልጅ ኀዘን የትናንቱን ሬሣ ዛሬ ያመለከዋል፤ ምሥጢሩንና ሥርዓቱንም ለወገኖቹ ያስተላልፋል።

16 ጊዜ ያልፋል፤ ባህልም ሕግ ይሆናል፤

17 ሐውልቶች ይመለኩ ዘንድ ያዘዙ ገዢዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ ርቀው የሚኖሩ በመሆናቸው በግንባር አክብሮታቸውን መግለጽ ላልቻሉት ሁሉ፥ የሚያከብሩትን ንጉሥ ምስል ያዩ ዘንድ፥ የገጽታው ንድፍ ተሠርቶ ይቀርብላቸው ነበር። ዓላማውም ከዓይነ የራቀውን በቅርብ እንዳለ ማስመሰል ነበር።

18 ገዢውን የማያውቁት ሰዎች እንኳን፥ በሠዓሊው ጥልቅ ስሜት በመገፋፋት፥ ለእርሱ ያላቸው አክብሬት እንዲስፋፋ ተደርጓል።

19 የኋለኛው ገዢውን ለማስደሰት ሲል፥ ያለ ጥርጥር በሰው ጥበብ ሁሉ በመጠቀም፥ ከእውነተኛው ገጽታ የተዋበ ምስል አቅርቧል።

20 ሕዝቡም በምስሉ ውበት ተታልሎ እንደ ሰው ያከበረውን፥ እንደ አምላክ ያመልከው ጀመር።

21 በዚህ ዓይነት በመጥፎ ዕድል ወይም በኃይል ተፅዕኖ የከበረውን የእግዚአብሔር ስም ለድንጋይና ለእንጨት በሰጡ ጊዜ የሰዎች ሕይወት በወጥመድ ገባች።


የአምልኮተ ጣኦት ውጤት

22 እነርሱ ስለ እግዚአብሔር ያላቸው የተሳሳተ አመለካከት ይኸው ብቻ አልነበረም፤ አላዋቂነት የወለደውን አስፈሪ የፍልሚያ ሕይወት እየመሩ፥ መቅሰፍቶቹን ሰላም ብሎ ይጠሯቸዋል።

23 ሕፃናትን የሚገድሉበት ሥርዓታቸው፥ መናፍስታዊ ምሥጢራቸው፥ ወይም የእብደት ሞፈራቸው፥ እንግዳ ባህላቸው፥

24 እንደሚያመለክቱት በአኗኗሯቸው ወይም በጋብቻዎቻቸው የቀራቸው ንጹሕና ጨርሶ የለም። አንዱ ሌላውን በተንኮል ሲገድል፥ ወይም ከሚስቱ ጋር ሲሴስን ይታያል።

25 የትም ቦታ በደም የተጨማለቀ ግድያ፥ ሌብነትና ማጭበርበር፥ ጉቦ፥ ውስልትና፥ ዓመጽ፥ የሐሰት ምስክርነት፥

26 ሰላማዊ ሰዎችን መበጥበጥ፥ ወሮታ ቢስ መሆን፥ ነፍስን ማሳደፍ፥ በተፈጥሮ ላይ ማመፅ ጋብቻን ማፋለስ፥ አመንዝራነትና ተስፋ መቁረጥ ይታያል።

27 ስማቸው ሊነሳ የማይገቡ ጣኦቶችን ማምለክ፥ የክፋት ሁሉ ምክንያት መነሻው፥ ማክተሚያውም ነውና።

28 ጣኦቶችን የሚያመልኩ ሰዎች፥ ፈንጠዝያቸው እስከ እብደት ይደርሶል፤ ወይም ትንቢታቸው ሐሰት ነው፤ በክፋትም ይኖራሉ፤ አልያም ያለ ማመንታት በሐሰት ይምላሉ።

29 የሚያምኑት ሕይወት በሌላቸው ጣኦቶት ስለሆነ የሐሰት መሐላዎቻቸው ሊጐዷቸው እንደሚችሉ አልተገነዘቡም።

30 ለዚህ ድርብ ወንጀል ግን ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፥ ጣኦቶችን በማምለክ እግዚአብሔርን አዋርደዋልና፤ ቅድስናውንም በመናቅ በተንኮል የሐሰት መሐላ አድርገዋልና።

31 የክፉ ሰዎችን በደል የሚከታተሉት፥ የሚምሉባቸው ጣኦቶች ሳይሆኑ፥ ለኃጡአተኞች የተወሰነው ቅጣት ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos