ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ይቆማሉ፤ ከጕድጓዱ እንደሚወጣ አውሬም ይነጥቃሉ፤ ይጮሃሉ፤ የሚድንም የለም።
ዘካርያስ 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸው ድምፅ ተሰምቶአል፣ የዮርዳኖስ ትዕቢት ተዋርዶአልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ተሰምቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ ክብራቸው ተገፍፏልና፤ የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸውን ድምፅ ስሙ! የዮርዳኖስ ጥቅጥቅ ደን ወድሟልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ስሙ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኞች ለምለም የሆነ መሰማሪያቸው ስለ ወደመ “ዋይ!” እያሉ ሲያለቅሱ ስሙ፤ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ ያለው የደን መኖሪያቸው ስለ ተደመሰሰ፥ አንበሶች በሐዘን ሲያገሡ ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸው ድምፅ ተሰምቶአል፥ የዮርዳኖስ ትዕቢት ተዋርዶአልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ተሰምቶአል። |
ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ይቆማሉ፤ ከጕድጓዱ እንደሚወጣ አውሬም ይነጥቃሉ፤ ይጮሃሉ፤ የሚድንም የለም።
ስማችሁንም እኔ ለመረጥኋቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ያጠፋችኋል፤ ባሪያዎች ግን በሐዲስ ስም ይጠራሉ።
የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም።
ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጼን አልተቀበላችሁም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል፤ በዚህም አልፈራችሁኝም።
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?”
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና እንደ አንበሳ ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወጣል፤ ጐልማሶቹንም ሁሉ በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቋቋም እረኛ ማን ነው?
እንዲህም በል፦ እናትህ ምን ነበረች? እንስት አንበሳ ነበረች፤ በአንበሶች መካከል ተጋደመች፤ በደቦል አንበሶችም መካከል ግልገሎችዋን አሳደገች።
የሰማርያ ሰዎች በቤትአዌን እንቦሳ አጠገብ ይኖራሉ፤ ሕዝቡ ያለቅሱለታል፤ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና እንዳዘኑበት እንዲሁ በክብሩ ደስ ይላቸዋል።
መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት! ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠውያ አገልጋዮች! ዋይ በሉ፤ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።
በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርስዋም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ጦርነት እንደ ወንዝ ይፈስሳል፤ እንደ ግብፅም ወንዝ ይሞላል፤ ደግሞም ይወርዳል።
በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።
አባቶቻችሁ ከነቢያት ያላሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው።