ሩት 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በሞዓብ ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘና እህል እንደ ሰጣቸው በሰማች ጊዜ፣ ሁለቱን ምራቶቿን ይዛ ወደ አገሯ ለመመለስ ከዚያ ተነሣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ጌታም ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እህልም እንደሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚ በሞአብ አገር ሳለች፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት እንዳደረገላቸውና ብዙ መከር እንደ ሰጣቸው ሰማች፤ ስለዚህ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከሞአብ ወደ እስራኤል ለመመለስ ተነሣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች። |
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፥ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ፥ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ያዕቆብም ባረካቸው፤ እንዲህም አለ፥ “አባቶች አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ ደስ ያሰኙት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥
ዮሴፍም የእስራኤልን ልጆች፥ “እግዚአብሔር በጐበኛችሁ ጊዜ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር አውጡ” ብሎ አማላቸው።
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተገለጠልኝ፦ መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፤ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
ሕዝቡም አመኑ፤ ደስም አላቸው፤ እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ጐብኝቶአልና፤ ጭንቀታቸውንም አይቶአልና፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ።
ብዙ ዝናምና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርን ለሚዘራ፥ እህልንም ለምግብ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፥ “እነሆ እህልንና ወይንን፥ ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።
የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፣ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ።
አንቺን ይጥሉሻል፤ ልጆችሽንም ከአንቺ ጋር ይጥሉአቸዋል፤ ድንጋይንም በደንጋይ ላይ አይተዉልሽም፤ የይቅርታሽን ዘመን አላወቅሽምና።”
ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
እግዚአብሔርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግመኛም ፀነሰች፥ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደች። ብላቴናው ሳሙኤልም በእግዚአብሔር ፊት አደገ።