ኤቲም ለንጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! በጌታዬም በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ! ጌታዬ ባለበት ስፍራ ሁሉ፥ በሞትም ቢሆን በሕይወትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገልጋይህ እሆናለሁ” አለው።
ሩት 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ እዚያው እቀበራለሁ። ከእንግዲህ ሞት ከሚለየን በቀር ብለይሽ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር ጌታ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፤ በዚያም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ እንዲሁም ይጨምርብኝ፤” አለች። |
ኤቲም ለንጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! በጌታዬም በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ! ጌታዬ ባለበት ስፍራ ሁሉ፥ በሞትም ቢሆን በሕይወትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገልጋይህ እሆናለሁ” አለው።
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋብዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳትጠልቅ እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ” ብሎ ማለ።
እግዚአብሔር ለዳዊት እንደ ማለለት እንዲሁ ከእርሱ ጋር ዛሬ ባላደርግ እግዚአብሔር በአበኔር ይህን ያድርግበት፤ ይህንም ይጨምርበት።
ከቀበሩትም በኋላ ልጆቹን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፥ “በሞትሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው በተቀበረበት መቃብር ቅበሩኝ፤ አጥንቶቼ ከአጥንቶቹ ጋር ይድኑ ዘንድ አጥንቶቼን በአጥንቶቹ አጠገብ አኑሩ፤
ኤልዛቤልም፥ “አንተ ኤልያስ ከሆንህ እኔም ኤልዛቤል ከሆንሁ ነገ በዚህ ጊዜ ሰውነትህን ከእነዚህ እንደ አንዱ ሰውነት ባላደርጋት፥ አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ” ብላ ወደ ኤልያስ ላከች።
ንጉሡም ሰሎሞን፦ እንዲህ ሲል በእግዚአብሔር ማለ። “አዶንያስ ይህን ቃል በሕይወቱ ላይ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ።
ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም በፊቱ አስቀምጡና፦ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው ይመስክሩበት፤ አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መትታችሁ ግደሉት።”
ንጉሡም፥ “የሣፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ዛሬ በላዩ ያደረ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርገኝ እንዲህም ይግደለኝ” አለ።
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን የጸጋውን ወንጌል እንዳስተምር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልሁትን ሩጫዬን እንድጨርስና መልእክቴንም እንድፈጽም ነው እንጂ ለሰውነቴ ምንም አላስብላትም።
ሩትም፦ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፣ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፣
አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ፥ እኔም ባላስታውቅህ፥ በሰላምም ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ፤ ይህንም ይጨምር፤ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።
ለናባልም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ብንተው፥ እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ፤ እንዲህም ይጨምር” ብሎ ነበር።
እርሱም፥ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? ከእኔ አትሸሽግ፤ ከነገረህና ከሰማኸው ነገር ሁሉ የሸሸግኸኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፤ እንዲህም ይጨምርብህ” አለው።