ሮሜ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኦሪት የተነሣ ኀጢአት ስለ ታወቀች ሰው ሁሉ የኦሪትን ሥርዐት በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት አይጸድቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሥጋ ለባሽ በርሱ ፊት ሊጸድቅ አይችልም፤ ይልቁንም በሕግ አማካይነት ኀጢአትን እንገነዘባለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። |
የሚምረኝ፥ መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና አዳኜ፤ መታመኛዬም፤ እርሱን ታመንሁ፤ ሕዝቡንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
አብርሃም፥ ዘሩም ዓለምን ይወርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦሪትን ሥራ በመሥራት አይደለም፤ በእግዚአብሔር ቃል፥ እርሱንም በማመን በእውነተና ሃይማኖቱ ይህን አገኘ እንጂ።
ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢአት ምን እንደ ሆነች ሳትታወቅ በዓለም ውስጥ ነበረች፤ ነገር ግን የኦሪት ሕግ ገና ስላልመጣ ኀጢአት ተብላ አትቈጠርም ነበር።
ይህስ ስለምን ነው? ጽድቃቸው የኦሪትን ሥራ በመሥራት እንጂ በእምነት ስለ አልሆነ ነው፤ የእንቅፋት ድንጋይ አሰነካከላቸው።
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ የኦሪትን ሥራ በመሥራት እንደማይጸድቅ እናውቃለንና፤ እኛም የኦሪትን ሥራ በመሥራት ሳይሆን በእርሱ በማመናችን እንጸድቅ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነናል፤ ሰው ሁሉ በኦሪት ሥራ አይጸድቅምና።
ኦሪት ምንም ግዳጅ አልፈጸመችምና፤ ነገር ግን በእርስዋ ፋንታ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ከእርስዋ የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።