Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አብ​ር​ሃም፥ ዘሩም ዓለ​ምን ይወ​ርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት አይ​ደ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እር​ሱ​ንም በማ​መን በእ​ው​ነ​ተና ሃይ​ማ​ኖቱ ይህን አገኘ እንጂ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱ የዓለም ወራሽ እንዲሆን አብርሃምና ዘሩ ተስፋን የተቀበሉት በሕግ በኩል አልነበረም፤ ነገር ግን በእምነት ከሆነው ጽድቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዓለምን እንዲወርስ ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለአብርሃምና ለዘሩ ዓለምን እንደሚወርስ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠው በእምነት ስላገኘው ጽድቅ ነው እንጂ ሕግን በመፈጸሙ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 4:13
15 Referencias Cruzadas  

ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ና​ች​ሁም እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋ​ውን የም​ት​ወ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እና​ንተ ናችሁ።


ልጆች እን​ዲ​ሆ​ኑት ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው፤ እነ​ዚህ ከሥጋ የተ​ወ​ለዱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች አይ​ደ​ሉም።


ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።


ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


እባ​ር​ካ​ታ​ለ​ሁና፥ ከአ​ን​ተም ልጆ​ችን እሰ​ጣ​ታ​ለ​ሁና፤ አሕ​ዛ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ከእ​ር​ስዋ ይወ​ጣሉ።”


የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህ​ንም እረ​ግ​ማ​ለሁ፤ የም​ድር ነገ​ዶ​ችም ሁሉ በአ​ንተ ይባ​ረ​ካሉ።”


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዴት ያው​ቃል? በአ​ር​ያ​ምስ በውኑ የሚ​ያ​ውቅ አለን?” ይላሉ።


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


“እኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ያና​ገ​ረ​ላ​ቸ​ውን ተስፋ እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን።


ለተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተ​ገ​ዘ​ሩት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ሳይ​ገ​ዘር እንደ አመነ ሳይ​ገ​ዘሩ የአ​ባ​ታ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን የሃ​ይ​ማ​ኖ​ቱን ፍለጋ ለሚ​ከ​ተሉ ደግሞ ነው እንጂ።


ወገ​ና​ቸው ላይ​ደለ ለእ​ርሱ ግን አብ​ር​ሃም ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው፤ እር​ሱም ተስፋ ያለው አብ​ር​ሃ​ምን ባረ​ከው።


ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios