La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የተ​ገ​ለ​ጠ​ለ​ትስ ምን አለው? “ለጣ​ዖት ያል​ሰ​ገዱ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስ​ቀ​ር​ቻ​ለሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር የሰጠው መልስ ግን ምን ነበር? “ጕልበታቸው ለበኣል ያልተንበረከከውን ሰባት ሺሕ ሰዎች ለራሴ አስቀርቻለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን መለኮታዊ መልስ ምን አለው? “ለበዓል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ብሎ መለሰለት? “ባዓል ለተባለው ጣዖት ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለራሴ አስቀርቻለሁ” ብሎታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።

Ver Capítulo



ሮሜ 11:4
12 Referencias Cruzadas  

በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት መሄድ አል​በ​ቃ​ውም፤ የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ን​ንም ንጉሥ የኤ​ያ​ት​ባ​ሔ​ልን ልጅ ኤል​ዛ​ቤ​ልን አገባ፤ ሄዶም በዓ​ልን አመ​ለከ ሰገ​ደ​ለ​ትም።


ኤል​ያ​ስም፥ “ሁሉን ለሚ​ገዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ቀን​ቻ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቃል ኪዳ​ን​ህን ትተ​ዋ​ልና፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ነቢ​ያ​ት​ህ​ንም በሰ​ይፍ ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ እኔም ብቻ​ዬን ቀር​ቻ​ለሁ ነፍ​ሴ​ንም ሊወ​ስ​ዱ​አት ይሻሉ” አለ።


እኔም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጕል​በ​ታ​ቸ​ውን ለበ​ዓል ያላ​ን​በ​ረ​ከ​ኩ​ትን ሁሉ፥ በአ​ፋ​ቸ​ውም ያል​ሳ​ሙ​ትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።”


በጽ​ዮን የቀሩ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ረፉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሕ​ይ​ወት የተ​ጻፉ ሁሉ፥ ቅዱ​ሳን ይባ​ላሉ።


እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ት​ንም፥ ወደ ልቤም ያል​ገ​ባ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ለበ​ዓል ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ የበ​ዓ​ልን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ሠር​ተ​ዋ​ልና፤


ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።


እር​ስ​ዋም እህ​ል​ንና ወይ​ንን ዘይ​ት​ንም የሰ​ጠ​ኋት፥ ብር​ንና ወር​ቅን ያበ​ዛ​ሁ​ላት እኔ እንደ ሆንሁ አላ​ወ​ቀ​ችም። እር​ስዋ ግን ወር​ቁ​ንና ብሩን ለጣ​ዖት አደ​ረ​ገች።


እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፣ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፣


እስ​ራ​ኤ​ልም ለብ​ዔል ፌጎር ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ።


ብዔ​ል​ፌ​ጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ለ​ውን ሰው ሁሉ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ለይቶ አጥ​ፍ​ቶ​ታ​ልና አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ዔ​ል​ፌ​ጎር ያደ​ረ​ገ​ውን ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትተው በዓ​ል​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።