Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ት​ንም፥ ወደ ልቤም ያል​ገ​ባ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ለበ​ዓል ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ የበ​ዓ​ልን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ሠር​ተ​ዋ​ልና፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እኔም ያላዘዝኋቸውን፣ ያልተናገርኋቸውን፣ ፈጽሞም ያላሰብሁትን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን በእሳት ሊሠዉለት ለበኣል መስገጃ ኰረብቶች ሠርተዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እኔም ያላዘዝሁትን ያልተናገርሁትንም ወደ ልቤም ያልገባውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አድርገው ለበዓል ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ልጆቻቸውንም መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል ለባዓል መሠዊያዎችን ሠርተዋል፤ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም፤ ከቶም ስለዚህ ነገር አላሰብኩም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እኔም ያላዘዝሁትን ያልተናገርሁትንም ወደ ልቤም ያልገባውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አድርገው ለበኣል ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና ስለዚህ፥

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 19:5
14 Referencias Cruzadas  

ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


ደግ​ሞም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለም​ስሉ ሠዋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛ​ብም ክፉ ልማድ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወር​ቄን በት​ነ​ሻ​ልና ከኀ​ጢ​አት ምኞት በሠ​ራ​ሽው ዝሙት ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽን ገል​ጠ​ሻ​ልና በሰ​ጠ​ሻ​ቸ​ውም በል​ጆ​ችሽ ደም፥


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ እን​ዲ​ያ​ውቁ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ማኅ​ፀን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ በአ​መ​ጡ​ልኝ ጊዜ፥ በመ​ባ​ቸው አረ​ከ​ስ​ኋ​ቸው።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገ​ባል፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም ታስ​ባ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፦


ከዘ​ር​ህም ለሞ​ሎክ አት​ስጥ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ስም አታ​ር​ክስ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


በነ​ጋ​ውም ባላቅ በለ​ዓ​ምን ይዞ ወደ በአል ኮረ​ብታ አወ​ጣው፤ በዚ​ያም ሆኖ የሕ​ዝ​ቡን አንድ ወገን አሳ​የው።


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos