መዝሙር 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኞች ወደ ሲኦል ይመለሱ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ሁሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ተገለጠ፥ ፍርድንም አከናወነ፥ ክፉ በገዛ እጆቹ ሥራ ተጠመደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ። እግዚአብሔርንም ከረሱ ሕዝቦች ጋር ይቀላቀላሉ። |
ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል፤ ለከንቱ ነገርም አጥነዋል፤ የቀድሞውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማማውና ወደ ሰንከልካላው መንገድ ለመሄድ በመንገዳቸው ተሰናከሉ።
የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ዐምጸዋልና፥ ቅዱስ አምላካቸውንም ረስተዋልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእስራኤል ልጆች ልቅሶና ጩኸትም ተሰማ።
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”