አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ይቅርታህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
የምትቈጣን ለዘላለም ነውን? ቍጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?
የመድኃኒታችን አምላክ ሆይ፥ መልሰን፥ ቁጣህንም ከእኛ መልስ።
በእኛ ላይ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን? ቊጣህንስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ታስተላልፋለህን?
በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስፋዬም ሆነኽልኛልና መራኸኝ።
አቤቱ አመሰግንሃለሁ፤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ፤ ተአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።
የኤፍሬም ልጆች ቀስታቸውን ገትረው ይወጉ ነበር። በሰልፍ ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አምላኬም ይሰማኛል።
በሰይፍ ስለት ይወድቃሉ፤ በአሕዛብም ሁሉ ይማረካሉ፤ የአሕዛብ ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ይረግጡአታል።
ስለዚህ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን መርገም ሁሉ ያመጣባት ዘንድ የእግዚአብሔር ቍጣ በዚህች ምድር ነደደ፤