በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፥ “ከተማቸውን የሚሠሩ እነዚህ ደካሞች አይሁድ ኀይላቸው ምንድን ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን?” ብሎ ተናገረ።
መዝሙር 83:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ ብፁዓን ናቸው፤ ለዓለምና ለዘለዓለም ያመስግኑሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤል ለዘለዓለም የተረሳ እንዲሆን ኑ፤ መንግሥታቸውን እንደምስስ” ይላሉ። |
በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፥ “ከተማቸውን የሚሠሩ እነዚህ ደካሞች አይሁድ ኀይላቸው ምንድን ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን?” ብሎ ተናገረ።
ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና፤ ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፤ ከዚህ ወደዚህ አቃዳው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፤ የምድር ኃጥኣን ሁሉ ይጠጡታል።
ኑ፤ እንጠበብባቸው፤ የበዙ እንደሆነ ጦርነት በመጣብን ጊዜ በጠላቶቻችን ላይ ተደርበው በኋላችን ይወጉናልና፥ ከምድራችንም ያስወጡናልና።”
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
“ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወገድ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘለዓለም ይቀራል።”
ከእንግዲህ ወዲህ የሞአብ ፈውስ የለም፤ በሐሴቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት” ብለው ክፉ ነገርን አስበውባታል። ፈጽሞ ትተዋለች፤ ከኋላዋ ሰይፍ ይመጣልና።
ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ እጅግ እንዳይስፋፋ ዳግመኛ በኢየሱስ ስም ሰውን እንዳያስተምሩ አጠንክረን እንገሥጻቸው።”