ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
መዝሙር 80:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተስ ብትሰማኝ የድንገት አምላክ አልሆንህም፥ ለሌላ አምላክም አትስገድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሬቱን መነጠርህላት፤ እርሷም ሥር ሰድዳ አገሩን ሞላች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፥ አሕዛብን አባረርህ እርሷንም ተከልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታድግበትን ቦታ መነጠርህላት፤ ሥሮችዋ በመሬት ውስጥ ጠልቀው መሠረት ያዙ፤ በምድሩም ላይ ተንሰራፋች። |
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ ይሁዳና እስራኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እያንዳንዳቸው ከወይኑና ከበለሱ በታች ተዘልለው ይቀመጡ ነበር።
ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ።
አጥር አጠርሁ፤ በዙሪያውም ቈፈርሁ፤ ድንጋዮችንም ለቅሜ አወጣሁ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከልሁ፤ በመካከሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማስሁለት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቅሁት፤ ዳሩ ግን እሾህን አፈራ።
አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥር ሰድደዋል፤ ወልደዋል አፍርተውማል፤ በአፋቸውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
በፊታችሁም ተርብ ሰደድሁ፤ በሰይፍህም፥ በቀስትህም ሳይሆን ዐሥራ ሁለቱን የአሞሬዎናውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደድኋቸው።