ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና።
የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነድደው፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?
አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የሕዝብህን ጸሎት ባለመቀበል ቊጣህን የምትገልጠው እስከ መቼ ነው?
በልባችን ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን፥ ከዘይትም ይልቅ በዛ።
ወዳጆችህም፥ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ ስማኝም።
በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስፋዬም ሆነኽልኛልና መራኸኝ።
አቤቱ አመሰግንሃለሁ፤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ፤ ተአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ይቅርታህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
ጸሎታችን እንዳያርግ ራስህን በደመና ከደንህ።
የእግዚአብሔር ቍጣ፥ ቅንአቱም በዚያ ሰው ላይ ይነድዳል እንጂ እግዚአብሔር ይቅርታ አያደርግለትም፤ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ በላዩ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።