ከስንዴም ስብ አበላቸው፥ ከዓለቱም ማር አጠገባቸው።
እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤ የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።
ቀኝህ እጅህ የተከለውን፥ ለራስህ ያጸናኸውን ልጅ ጠብቅ።
ጠላቶች ቈራርጠው በእሳት አቃጥለዋታል፤ በቊጣህ ተመልከታቸው፤ አጥፋቸውም!
አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ።
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
በአጠገብህ ሺህ፥ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርቡም።
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
በእኔ የማይኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጥሉታል፤ ሰብስበውም በእሳት ያቃጥሉታል።
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።