መዝሙር 80:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ጠላቶችስ ዋሽተውት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘለዓለም ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ቡቃያ፣ ለራስህ ያጸደቅሃት ተክል ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፥ ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥ ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችን አንተ የተከልካትን ተንከባክበህም ያሳደግኻትን የወይን ግንድ ጠብቃት! |
አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ፥ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባርያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የፈጠረኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
ከሰማይ ተመለስ፤ ከቅድስናህና ከክብርህ ማደሪያም ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህስ ወዴት ነው? የቸርነትህና የይቅርታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለሃልና።
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።
በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
ከቅዱስ ማደርያህ ከሰማይ ጐብኝ፤ ሕዝብህንም እስራኤልን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ትሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን እንደ ማልህላቸው የሰጠሃቸውንም ምድር ባርክ።