እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
መዝሙር 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፥ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፈጠርካቸው ፍጥረቶች ሁሉ ላይ፥ ገዢ አድርገህ ሾምከው፤ ከፍጥረትም ሁሉ በላይ አደረግኸው። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር አራዊት፥ በሰማይ ወፎች፥ በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱትም፥ በባሕር ዓሦችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነርሱንም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ።
ሁሉንም ከእግሩ በታች አድርገህ አስገዛህለት።” ሁሉን ለእርሱ ባስገዛለት ጊዜም የተወውና ያላስገዛለት የለም፤ አሁን ግን ሁሉን እንዳስገዛለት አናይም።