የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተውም ለልጆቻቸው ይነግራሉ።
ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ ከልቤም ጋራ ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፤
የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፥ የጥንቱን ዓመታት አሰብሁ፥
ሌሊቱን የማነጋው በጥልቅ ሐሳብ ነው፤ ሳሰላስል ሳለሁ ራሴን የምጠይቀው እንዲህ እያልኩ ነው፤
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ኀጢኣተኛ እንድሆን አታስተምረኝ፤ ለምንስ እንደዚህ ፈረድህብኝ?
ነገር ግን በሌሊት ጥበቃን የሚያዝዝ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም፤
ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል፤ ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል።
አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
ተቈጡ፥ ነገር ግን አትበድሉ፤ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ።
እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ላይ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አበዛሁ፤ ልቤንም ለጥበብና ለዕውቀት ሰጠሁ፥” በማለት ተናገርሁ።
ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክፋታቸውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥቶአልና ለእነርሱ ስበክ።”
በመንፈቀ ሌሊትም ጳውሎስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርንም በዜማ አመሰገኑት፤ እስረኞቹም ይሰሙአቸው ነበር።
የዱሮውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ይነግርህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፤ ይተርኩልህማል።