እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
መዝሙር 76:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ዛሬ ጀመርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እንደሚያፈራርቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ቊጣ አንተን ያመሰግንሃል፤ ከጦርነት የተረፉትም በዓልህን ያከብራሉ። |
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
እግዚአብሔርም ለፈርዖን በመጽሐፍ እንዲህ አለው፥ “ኀይሌን በአንተ ላይ እገልጥ ዘንድ፥ ስሜም በምድር ሁሉ ይሰማ ዘንድ ስለዚህ አስነሣሁህ።”
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”